የመኢአድ መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 20.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የመኢአድ መግለጫ

መኢአድ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው መግለጫ በተለይ በደቡብ ክልልና በአሶሳ አካባቢ አባላቶቹ ላይ የሚካሄደው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል ። በአባላቶቹ ላይ ስለ ሚፈፀመው የመብት ረገጣ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም ሆነ ለሰብአዊ መብት ድርጅቶች ቢያሳውቅም ችግሩ አለመወገዱን መኢአድ ተናግሯል ።

ተቃዋሚው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በምህፃሩ መኢአድ በአባላቱና በደጋፊዎቹ ላይ ተፈፀመ የሚለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ና አፈና እንዲቆም ጠየቀ ።  መኢአድ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው መግለጫ በተለይ በደቡብ ክልልና በአሶሳ አካባቢ አባላቶቹ ላይ የሚካሄደው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል ። በአባላቶቹ ላይ ስለ ሚፈፀመው የመብት ረገጣ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም ሆነ ለሰብአዊ መብት ድርጅቶች ቢያሳውቅም ችግሩ አለመወገዱን የመኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ተናግረዋል ። መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ያቀርብልናል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic