የመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን | አፍሪቃ | DW | 15.04.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን

አሁንም በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን ስደተኞች አጠብቂኝ ዉስጥ እንደሚገኙ እያስታወቁ ነዉ

ሳዑዲ አረቢያ መራሹ ጦር የመንን መደብደብ ከጀመረ ጀምሮ በርካታ መንግሥታት የመን ይኖሩ የነበሩ ዜጎቻቸዉን ወደየሐገራቸዉ መልሰዋል።ወይም እየመለሱ ነዉ።ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችም ዕርዳታ እንዲደረግላቸዉ በየጊዜዉ እየጠየቁ ነዉ።የኢትዮጵያ መንግሥትና ዓለም አቀፉ የስደተኞችን ጉዳይ ድርጅት (IOM) ኢትዮጵያዉያኑን ከየመን ማስወጣት መጀመራቸዉን በተደደጋጋሚ እስታዉቀዋል።ይሁንንና አሁንም በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን ስደተኞች አጠብቂኝ ዉስጥ እንደሚገኙ እያስታወቁ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይን አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic