የመን ከአሊ አብደላ ሳሌሕ በኋላ | ዓለም | DW | 05.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የመን ከአሊ አብደላ ሳሌሕ በኋላ

የቀድሞው የየመን ፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳሌሕ ሞት አገሪቱን ከመንታ መንገድ ላይ ጥሏታል። ለአራት አስርት አመታት በየመን ፖለቲካ ላይ ቁልፍ ሚና የነበራቸው ሳሌሕ አምባገነን እና በየጊዜው ጠላት እና ወዳጆቻቸውን የሚቀያይሩ ቢሆኑም እንኳ ሞታቸው በየርስ በርስ ጦርነት ለተዘፈቀችው የመን መርዶ ሆኗል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:01

ሳሌሕ በሑቲ አማፅያን የተገደሉት ባለፈው ሰኞ ነበር

የቀድሞው የየመን ፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳሌሕ ሞት አገሪቱን ከመንታ መንገድ ላይ ጥሏታል። ለአራት አስርት አመታት በየመን ፖለቲካ ላይ ቁልፍ ሚና የነበራቸው ሳሌሕ አምባገነን እና በየጊዜው ጠላት እና ወዳጆቻቸውን የሚቀያይሩ ቢሆኑም እንኳ ሞታቸው በየርስ በርስ ጦርነት ለተዘፈቀችው የመን መርዶ ሆኗል። ከሞታቸው ሶስት ቀናት በፊት የሶስት አመታት አጋራቸውን ሑቲዎች ፊት ነስተው ከሳዑዲ የሻከረ ወዳጅነታቸውን ለማደስ ዳር ዳር እያሉ ነበር። እንደ ተንታኞች አባባል ግን "ቁማራቸው" አልሰራም። የሑቲዎቹ መሪ አብድል ማሊክ አል-ሑቲ የቀድሞው የየመን ፕሬዝዳንት የተገደሉት በአገር "ክሕደት" ተወንጅለው መሆኑን ተናግረዋል። የመን የሚገኘው ግሩም ተክለኃይማኖት እንደሚለው የሳሌሕ ሞት ከተሰማ በኋላ ሰንዓ ሐዘን ተጭኗታል። ለመሆኑ የአሊ አብደላ ሳሌሕ ሞት በየመን የርስ በርስ ጦርነት ላይ ምን ትርጉም አለው? 
ግሩም ተክለኃይማኖት
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic