1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመንግሥት ስልጣን ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ሰባት ተቃዋሚዎች አማራጭ ሃሳብ አቀረቡ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 4 2012

የኢትዮጵያ መንግሥት የአስፈጻሚው አካል ስልጣን ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ኦነግን ጨምሮ 7 የፖለቲካ ፓርቲዎች   አማራጭ ነው ያሉትን ሃሳብ አቅርበዋል። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው እንዳመለከቱት የአስፈጻሚው አካል በአንድ አመት ቆይታው  የመንግስትን የዕለት ተዕለት ተግባር እያከናወነ እንዲቆይ ይሁንታቸውን ሰጥተዋል።

https://p.dw.com/p/3c7Ry
Kejela Megersa
ምስል DW/S. Getachew

ሰባት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሌላ አማራጭ ይዘው መጥተዋል

 

የኢትዮጵያ መንግሥት የአስፈጻሚው አካል ስልጣን ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ኦነግን ጨምሮ 7 የፖለቲካ ፓርቲዎች   አማራጭ ነው ያሉትን ሃሳብ አቅርበዋል። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው እንዳመለከቱት የአስፈጻሚው አካል በአንድ አመት ቆይታው  የመንግስትን የዕለት ተዕለት ተግባር እያከናወነ እንዲቆይ ይሁንታቸውን ሰጥተዋል። ነገር ግን በስልጣን ላይ የሚቆየው መንግስት አዲስ ሕግ ማውጣትም ሆነ በስራ ላይ ያሉትን ሕጎችን የመሻር ስልጣን አይኖረውም ብለዋል።ውሳኔው በአንድ ግለሰብ በሚወሰን ውሳኔ ሌላ ሀገራዊ  ችግር ከሚያስከትል የፖለቲካ ፓርቲዎች የመፍትሄው አካል መሆናቸውን ያሳዩበት እንደሆነ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር  ኦነግ በተናጥል አስታውቋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ታምራት ዲንሳ 

አዜብ ታደሰ