የመንግሥት ማሳሰቢያ አድማ ለመቱ እጩ ሐኪሞች  | ኢትዮጵያ | DW | 20.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የመንግሥት ማሳሰቢያ አድማ ለመቱ እጩ ሐኪሞች 

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ከእጩ ሐኪሞቹ ጋር በተደረገ ውይይት አብዛኞቹ ወደ ትምህርታቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል። ያልተመለሱት በዚሁ አቋማቸው የሚጸኑ ከሆነ ከግማሽ የትምህርት አመት እስከ 1 አመት ድረስ ከትምህርታቸው የመታገድ እና እስከ መጨረሻው የመባረር ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላልም ሲሉ አሳስበዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:09

የመንግሥት ማሳሰቢያ

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ጥያቄዎቻችን ይመለሱ በሚል ትምህርት አድማ ላይ የነበሩ የተወሰኑ የዩኒቨርሲቲ እጩ ሐኪሞች አሁንም ወደ ትምህርታቸው አለመመለሳቸውን ገልጿል። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ከእጩ ሐኪሞቹ ጋር በተደረገ ውይይት አብዛኞቹ ወደ ትምህርታቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል። ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱት በዚሁ አቋማቸው የሚጸኑ ከሆነ ከግማሽ የትምህርት አመት እስከ አንድ አመት ድረስ ከትምህርታቸው የመታገድ ከፍ ካለም እስከ መጨረሻው የመባረር ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላልም ሲሉ አሳስበዋል። ቅጣቱ ተግባራዊ የሚሆነውም የየዩኒቨርሲቲዎቹ ሴኔት በሚያሳልፈው ውሳኔ መሠረት መሆኑን ሚኒስትር ዴታው ተናግረዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል፤


ሰሎሞን ሙጬ
 ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ 

Audios and videos on the topic