የመንና ያልሠመረው ሽምግልና፣ | ዓለም | DW | 23.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የመንና ያልሠመረው ሽምግልና፣

ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳሌህ፣ ከሥልጣን መንበር ከወረዱ ፤ የመን በእርስ-በርስ ጦርነት እንደምትማቅቅና የአል ቓኢዳ መፈንጫ እንደምትሆን ከመለፈፍ ካለመቦዘናቸውም፤

default

ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳሌህን የሚቃወም የህዝብ ሰልፍ፣ በሰንዓ፣

አሁንም ለ 3ኛ ጊዜ ሽምግልናው እንዳይሠምር አደናቅፈውታል። በተባበረው የዐረብ አሚሮች ኅብረት ኤምባሲ ቅጽር ግቢ የተጠበቀው የዕርቀ ሰላም ስምምነት ሳይሳካ ቀርቷል። የባህር ሰላጤው አገሮች ፤ አደራዳሪው ተወካይ፣ እንዲሁም የአሜሪካና የአውሮፓ አምባሳደሮች በቦታው ተገኝተው ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳሌህን በመጠባበቅ ላይ ሳሉ፤ የታጠቁ የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ለ 2 ሰዓት መፈናፈኛ አሳጥተው እንደነበረ ተመልክቷል። ዝርዝሩን ነቢዩ ሲራክ

ነቢዩ ሲራክ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ