የመናገር ነፃነት ሽልማት ለኢትዮጵያውያን | ኢትዮጵያ | DW | 20.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የመናገር ነፃነት ሽልማት ለኢትዮጵያውያን

«ከአራቱ ጋዜጠኞች ሶስቱ ደጋግመን አጠቃቀሙ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ባነሳነዉ የፀረ ሽብር ህግ ተፈርዶባቸዉ እስር ቤት ይገኛሉ። የእነሱ በነፃነት ሃሳብን የመግለፅ ሙከራ አሳሳቢና ትኩረት የሚያሻዉ መሆኑን አስተዉለናል። መስፍን ነጋሽ ከሃገራቸዉ ለመሰደድ የተገደዱ በርካታ ጋዜጠኞችን ይወክላል።» ሂዩመን ራይትስ ዋች

4 ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ሄልማን ሃሜት የተባለው የአለም ዓቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሂዩመን ራይትስ ዋች ሽልማት ተሰጣቸው ። በእስራ ላይ ያሉት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፣ ውብሸት ታዮ እና ርዕዮት አለሙ እንዲሁም ከሃገር የተሰደደው ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ድርጅቱ ዘንድሮ ይህን ሽልማት ከሰጣቸው 41 ፀሃፊዎች መካከል ይገኙበታል ። ድርጅቱ 4 ቱን ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች የሸለመው ጋዜጠኞች በሙያቸው ምክንያት የደረሰባቸውን ስቃይና የሚሰሩበትን ሁኔታ አጉልቶ ለማሳየት መሆኑን አስታውቋል ።
የሸላሚው የአለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ የሂዩመን ራይትስ ዋች የአፍሪቃ ጉዳዮች ተመራማሪ ላቲሻ ቤደ እንዳሉት የሄልማን ሃሜት ሽልማት የሚሰጠው በየሃገሩ የመናገር ነፃነትን በማራመድ በግል ጥረት ላደረጉና ተምሳሌት ለሆኑ ፀሃፊዎች ነው ። ሽልማቱም እንደ ተሸላሚው የሚለያይ የገንዘብ ስጦታን ያካትታል ። በየአመቱ የሚበረከትው ይህ ሽልማት ዘንድሮ በአለም ዙሪያ ለሚገኙ 41 ፀሃፍት ተሰጥቷል ። ከመካከላቸው 4 ቱ ኢትዮጵያውያኑ ጋዜጠኞች በእስር ላይ የሚገኙት እስክንድር ነጋ ፣ ውብሸት ታዮና ርዕዮት አለሙ እንዲሁም በስደት ላይ ያለው ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ናቸው ። ድርጅቱ እነዚህን ጋዜጠኞች የሸለመበትን ምክንያት ላቲሻ ቤደ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

--- DW-Grafik: Per Sander 2010_11_24_symbolbild_pressefreiheit.psd


« ሽልማቱ የተሰጣቸው በኢትዮጵያ የነፃ ጋዜጠኞችን እጣ ፈንታ አጉልቶ ለማሳየት ነው ። 4ቱ ግለሰቦች በግልፅ እንደሚታወቀው የመገናኛ ብዜሃን ነፃነት እጅግ በተገደበበት ሃገር የመናገር ነፃነትን በማራመድ በግላቸው ብዙ ስቃይ ደርሶባቸዋል ። ከዚህ በተጨማሪም በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ገፅታም አጉልቶ ለማሳየትም ነው »
ከሽልማቱ መስፈርቶች ውስጥ ፀሃፊዎች ወይም ጋዜጠኞች በሃገራቸው ያላቸው እውቅና እና በሙያቸው ያገለገሉበት ዘመንም ይካተታል ። የከፈሉት መስዋዕትነት እንዲሁ ከግምት ውስጥ ይገባል ።
«በድጋሚ ማጉላት የምንፈልገዉ ከአራቱ ጋዜጠኞች ሶስቱ ደጋግመን አጠቃቀሙ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ባነሳነዉ የፀረ ሽብር ህግ ተፈርዶባቸዉ እስር ቤት ይገኛሉ። የእነሱ በነፃነት ሃሳብን የመግለፅ ሙከራ አሳሳቢና ትኩረት የሚያሻዉ መሆኑን አስተዉለናል። መስፍን ነጋሽ በግድ ከሃገራቸዉ ለመሰደድ የተገዱ

--- DW-Grafik: Per Sander 2010_11_30_gefährliches_leben_journalisten.psd

በርካታ ጋዜጠኞችን ይወክላል። የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዉ CPJ እንደሚለዉ በርካታ ጋዜጠኞች ከየሀገራቸዉ እየተሰደዱ ነዉ። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ከሶማሊያና ኢራን ቀጥላ ጋዜጠኞቿን ለስደት በመግፋት በሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። »
HRW በኢትዮጵያ የፕሬስ ይዞታ እንዲሻሻልና የታሰሩ ጋዙጠኞችም እንዲለቀቁ በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ ከሚያስተላልፉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አንዱ ነው ። ድርጅቱም እንደሚለው የሚያሳስበው እስካሁን ከመንግስት በጎ ምላሽ አለማግኘቱ ብቻ ሳይሆን የፍትህ አካላት እርምጃም ነው ።

Human Rights Watch Logo


« አሳሳቢው ጉዳይ የመንግሥት መልስ ብቻ አይደለም ። ይልቁንም በየጊዜው እንደሚንፀባረቀው እነዚህ ጉዳዮች ምን ያህል ፖለቲካዊ እንደሆኑ ነው ። በተጨማሪም ፍርድ ቤት የጋዜጠኞቹን ክስ ሲያዳምጥና

business conference camera journalism © picsfive #16855152

ውሳኔ ሲሰጥ ነው የከረመወ በአሁኑ ጊዜ አሳዛኙ ውጤት የኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት የፖለቲካ መሪዎች ናአመራር መሣሪያ መሆኑ ነው ። የፍርድ ቤቶችና ዳኞች ሃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ እንዲወጡ ህገ መንግሥቱም በትክክል ተግባራዊ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባቸዋል »  
4 ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ያገኙት ሄልማን ሃሜት የተባለው ሽልማት በፀረ ኮምኒዝም የምርመራ ዘገባዎቻቸው ምክንያት በ1960ዎቹ ጫናና ወከባ ይደርስባቸው ለነበሩት አሜሪካውያኑ ፀሃፍት ሊሊያን ሄልማን ና  ሃሜት መታሰቢያ የሚበረከት ሽልማት ነው ። ሽልማቱ የሚሰጠውም በአለም ዙሪያ የፖለቲካ ጥቃት ሰለባ ለሆኑና የገንዘብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ፀሃፊዎች ነው ።  

 

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic