የመብት ጥሰትና የተወካዮች ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ዉሳኔ  | ኢትዮጵያ | DW | 25.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የመብት ጥሰትና የተወካዮች ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ዉሳኔ 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከሰኔ 2008 ዓ/ም መጀመርያ ጀምሮ እስከ መስከረም 2008 መጨረሻ ድረስ በኦሮሚያ፣ በአማራና በደቡብ ክልል ተከስቶ ሥለነበረዉ ተቃዉሞና ግጭት ያደረገዉን ጥናት ዉጤት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ማቅረቡ ይታወሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:06

የቋሚ ኮሚቴ ዉሳኔ

ኮሚሽኑ የ669 ሰዎች ህወት ማለፉን ገልፆ የፀጥታ አካላቱም «ተመጣጣኝ የሃይል ርምጃ» እንደወሰዱ አስታዉቀዋል።

ምክርቤቱም በዘገባዉ ላይ የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዉሳኔ እንዲሰጥበት ማስተላለፉም ተዘግበዋል። መያዝያ 12 ኮሚቴዉ በተቀዉሞ ወቅት «ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ» የመንግስት ባለስልጣናት እና «ከመጠን ያለፈ» ርምጃ የወሰዱት የፀጥታ አስከባርዎች  «በሕግ እንዲጠየቁ» ዉሳኔ ማስተላለፉም የኮሚቴዉ ሰብሳቢ አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

የአንድም ሰዉ «ከህግ ዉጭ» ህወቱን ማጣት እንደለለበት የሚናገሩት አቶ ጰጥሮስ የፀጥታ አስከባሪዎች «ተመጣጣኝ ርምጃ» ነዉ የወሰዱት የሚለዉ «በህግ የተሰጠዉን ትርጉም» ተከትሎ ነዉ ይላሉ። ግን ከትርጉሙ ባለፈ ርምጃ የወሰዱት የፀጥታ አካል ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ አክለዉ ተናግረዋል። 
በአገርቱ እንድ አይነት ክስተት ሲፈጠር የመንግስት ባለስልጣናትም ሆነ የጸጥታ አካሉ በህግ ፊት ቀርቦ ሲጠየቁ አልታዝብንም፣ ስለዝህ አሁንም «ተፈፃሚ» መሆኑ ያጠራጥራል ብሎ የሚከራከሩ ወገኖች አልጠፉም። ይህን አቶ ጰጥሮስ እንደት ይመለከቱታል?

ተቃዋሚዎቹ  የኦሮሞ ፌዴራልስት ኮንግሬስ/ኦፌኮ/ና  ሰማያዊ ፓርቲም በተቃቁዉሞ ወቅት  ሰዎችን «አነሳስተዋል» በሚል ለተከሰተዉ ግጭት በህግ መጠየቅ እንዳለባቸዉ ኮምቴዉ መወሰኑን ለመረዳት ተችሏል።

መያዝያ 5 ቀን 2006 ዓ/ም ጀምሮ ኦሮሚያ ዉስጥ ችግር እንዳለ እሱም በሰላማዊ መንግድ መንግስት መፍታት እንዳለበት አቤቱታ ማቅረባቸዉን የሚናገሩት የኦፌኮ ምክትል ሊቀምንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ፓርትያቸዉ «በግርግር ስልጣን የመያዝ እቅድ እንደለለዉ» ይናገራሉ።

የሰማያዊ ፓርት ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ የኮምቴዉ ዉሳኔም ሆነ የኮሚሽኑ ዘገባ የገዢዉ ፓርቲ ተፅኖ እንዳለበት በግልጽ ይታያል ይላሉ።

የፌስ ቡክ ተከታታዮቻችን ሥለ ጉዳዩ አወያይተን ነበር።ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የኮምሽኑ ዘገባ «ሚዛናዊ ነዉ» ያሉን ነበሩ።ሌሎች ግን  መንግስት ሁለቱን ተቃዋሚወች «ለማዳከም» አቅዷል ይላሉ። የመንግስት ባለስልጣናት የጸጥታ አካሉ ላይ የህግ ርምጃ ተፈፃሚ መሆኑን በጥርጣሬ እንደሚመለከቱም ያጋሩን አሉ። «ገዳዩም፣ ፈራጁም፣ አጣሪዉም» መንግስት በመሆኑ ነዉ ስሉ አስተያየታቸዉን አጋርተዉናል።

 

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሀመድ


 

Audios and videos on the topic