የመቀሌዎች ዉዝግብ | ኢትዮጵያ | DW | 11.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የመቀሌዎች ዉዝግብ

ተማሪዎች እና ወላጆች እንደሚሉት በትምሕርት ቤቱ ሕንፃ ላይ የመለስ ፎቶ ግራፍ የተለጠፈዉ  የአፄ ዮሐንስን ታሪክ ለማንኳሰስ ነዉ። የትምሕርት ቤቱ ዳይሬክተር ግን ተቃራኒዉን ነዉ የሚሉት።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:55

የመቀሌዎች ዉዝግብ

መቀሌ-ትግራይ በሚገኘዉ የንጉሠ-ነገሥት አፄ ዮሐንስ አራተኛ መታሰቢያ መሰናዶ ትምሕርት ቤት ሕንፃ ላይ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ፎቶ ግራፍ መለጠፉ የከተማዋን ነዋሪዎች እያወዛገበ ነዉ።ተማሪዎች እና ወላጆች እንደሚሉት በትምሕርት ቤቱ ሕንፃ ላይ የመለስ ፎቶ ግራፍ የተለጠፈዉ  የአፄ ዮሐንስን ታሪክ ለማንኳሰስ ነዉ።የትምሕርት ቤቱ ዳይሬክተር ግን ተቃራኒዉን ነዉ የሚሉት።ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ሌሎች ነዋሪዎች ደግሞ የመለስን ስምና ዝና ለማጉላት ሲባል መቀሌ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አካባቢዎችም በሌሎች የታሪክ ሰዎች ስም የተሰየሙ ተቋማት በመለስ ስም እየተተኩ ነዉ ይላሉ።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic