ማስታወቂያ
የመስከረም 12 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና በድምጽ
ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ አዲስ አበባ ውስጥ እየተነጋገሩ ነው። ኢትዮጵያ 4ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በተሳካ መልኩ ማጠናቀቋን ተከትሎ ግብጽ ሕገወጥ በማለት ጉዳዩን ተቃውማ ነበር።
በማዕከላዊ የሶማልያ ግዛት በቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን የሃገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ። ፍንዳታው በመኪና በተጠመደ ቦምብ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።
በናይጄሪያ መሳሪያ የታጠቁ ሽፍቶች ከ30 በላይ ስቪሎችን ማገታቸውን ተሰማ። ከታጋቾቹ 24ቱ ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው ተብሏል።
የሮማው ካቶሊክ ቤተክርስትያን ሊቀጳጳስ ፍራንሲስ አውሮጳውያን ስደተኞችን እንደወራሪ ማየት የለባቸውም አሉ። ይልቁንም መልካም አቀባበል ሊያደርጉላቸው ይገባል ሲሉም መክረዋል።
ዩክሬይን በጥቁር ባሕር የሩስያ የባሕር ሃይል ማዘዣ ጣቢያ ባካሄደችው የሚሳይል ጥቃት አንድ የባሕር ሃይል ከፍተኛ አዛዥን ጨምሮ በአስራዎቹ የሚቆጠሩ ወታደሮች መግደሏን አስታወቀች።