የመስቀል በዓል በድሬዳዋ የኑሮ ውድነት አጥልቶበት ተከብሯል | ኢትዮጵያ | DW | 27.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የመስቀል በዓል በድሬዳዋ የኑሮ ውድነት አጥልቶበት ተከብሯል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተካተዮች ዘንድ በየአመቱ በሚከበረው የመስቀል በዓል ዋዜማ የተከናወነው ደመራን ጨምሮ በዓሉ በድሬደዋ በደመቀ መልኩ ተከብሯል፡፡ አንድ የበአሉ ታዳሚ በዓሉን በመረዳዳት እና ይበልጥ አንድነትን በመጠበቅ ማክበር ይገባል ብለዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:09

የመስቀል በዓል በድሬዳዋ ከተማ ከዳመራው ዕለት አንስቶ በድምቀት ተከብሯል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተካተዮች ዘንድ በየአመቱ በሚከበረው የመስቀል በዓል ዋዜማ የተከናወነው ደመራን ጨምሮ በዓሉ በድሬደዋ በደመቀ መልኩ ተከብሯል፡፡ አንድ የበአሉ ታዳሚ በዓሉን በመረዳዳት እና ይበልጥ አንድነትን በመጠበቅ ማክበር ይገባል ብለዋል፡፡

አቶ አስቻለው የተባሉ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየናረ የመጣው የኑሮ ውድነት እና የምርቶች ዋጋ መጨመር ለበዓሉም ፈታኝ መሆኑን ገልፀው መንግስት በተለይ በዚህ ረገድ ትኩረት መስጠት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

የኮሮና ስርጭት ፣ የኑሮ ውድነት ፣ ለወራት የዘለቀ ጦርነት እና የዜጎች መፈናቀል እና ጉስቁልና እየፈተናት ባለወችው ኢትዮጵያ ከአንድ ሳምንት በኃላ መንግስት ይመሰረታል፡፡ መምህር ስንታየሁ አበራ የተባሉ አስተያየት ሰጭ እነዚህን ሁሉ ችግሮች ተቋቁሞ መንግስት መመስረት መቻሉ ትልቅ ውጤት መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ ተስፋ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ሶስት አመታት በርካታ ፈታኝ ሁኔታ እንደነበር የተናገሩት አቶ አስቻለው በበኩላቸው አሁንም ባለው ጦርነት ሳቢያ በርካቶች በቤታቸው በዓል ማክበር አለመቻላቸውን በመጥቀስ መንግስት ይህን ሁኔታ በአፋጣኝ መቋጨት አለበት ብለዋል፡፡

በየደረጃው በሀገሪቱ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍና ህብረተሰቡ በተረጋጋ ሁኔታ ህይወቱን መምራት የሚችልበትን ሁኔታ በመፍጠር በኩል አዲስ የሚመሰረተው መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic