የመሬት ባለቤትነት እና የምግብ ዋስትና | ኤኮኖሚ | DW | 20.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የመሬት ባለቤትነት እና የምግብ ዋስትና

ኤል-ኒኖ በተሰኘው የአየር ንብረት ክስተት ምክንያት በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ አስከፊነት ጨምሯል። እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከሆነ ድርቁም ይሁን የምግብ እጥረቱ ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት ገጥሟት የሚያውቅ አይነት አይደለም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:14

የመሬት ባለቤትነት እና የምግብ ዋስትና

የአስቸኳይ ርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ 3 ሚሊዮን ወደ አስር ሚሊዮን በላይ ያሻቀበ ሲሆን አብዛኞቹ ደግሞ ኑሯቸውን በእርሻ የሚመሩ ገበሬዎች ናቸው።ድርቁ በግብርና ላይ በከፍተኛ ደረጃ በግብርና ዘርፉ የእርሻ ሥራ እና የከብት እርባታ ላይ ጥገኛ በሆነው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አሌ የሚባል ባይሆንም ጫናው ምን ያክል ሊሆን እንደሚችል እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም። ለ85 በመቶ ኢትዮጵያውያን ሥራ የፈጠረው እና ለአጠቃላይ እና ከአገሪቱ ዓመታዊ ምርት (Gross Domestic Product) 50 በመቶ ድርሻ ያለው የግብርናው ዘርፍ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ተስኖታል። የመሬት ባለቤትነትን ማረጋገጥ ለምግብ ዋስትና ምን ያክል ጠቀሜታ ይኖረዋል?

እሸቴ በቀለ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic