የመሬት ቅርምትና እና የምግብ ዋስትና ዕጦት | ዓለም | DW | 15.10.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የመሬት ቅርምትና እና የምግብ ዋስትና ዕጦት

በመልማት ላይ ባሉ ሐገራት ተጨማሪ ምርት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየተባለ መሬት ለዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች በረዥም ጊዜ ኪራይ ወይም በሽያጭ መቸብቸቡ እንደቀጠለ ነው ።

በዚህ የመሬት መቀራመትም ለነዳጅ ምርት ወይም ለከብቶች መኖ የሚሆኑ ሰብሎችን ለማምረት ሰፊ ቦታ ስለሚወስድ የአገሬው ተወላጅ ገበሬዎች እምብዛም ቦታ የላቸውም። ዳቦ ለዓለም የተሰኘው የጀርመን ወንጌላውያን የዕርዳታ ድርጅት እና FIAN በሚል ምህፃር የሚታወቀው መረጃ አቅራቢው የሰብዓዊ መብት ድርጅት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ በሚል ፈሊጥ የተጀመረው የመሬት መቀራመት አደገኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አሳስበዋል። ነገ የሚታሰበውን የዓለም የምግብ ቀን ምክንያት በማድረግ ድርጅቶቹ የዓለማችንን ረሀብተኛ ቁጥር ለመቀነስ ትራፊ ለማጋባሰ ከሚወሰድ ዕርምጃ ይልቅ በሀገር ውስጥ አስፈላጊ ለሆነ ምርት ቅድሚያ እንዲሰጥ አስገንዝበዋል ።

Sabine Ripperger

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ