የመረጃ ቴክኖሎጂ አጠባበቅ | ኤኮኖሚ | DW | 12.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የመረጃ ቴክኖሎጂ አጠባበቅ

በጀርመናዊቷ የሀኖፈር ከተማ ባለፈው እሁድ የተከፈተው እና አምስት ቀናት የሚቆየው ትልቁ የኮምፒውተር ትርዒት የመረጃ ቴክኖሎጂን አጠባበቅ እንዴት አስተማማኝ ማድረግ ይቻላል ለሚለው ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶዋል።

በመረጃ አጠባበቅ ላይ የሚታየው አሰራር፣ በተለይ፣ አሜሪካዊው ኤድዋርድ ስኖውደን ያጋለጠው የዩኤስ አሜሪካ ብሔራዊው ፀጥታ ድርጅት ፣

በምሕፃሩ «ኤን ኤስ ኤ» ግለሰቦችን ፣ ያገር መሪዎችን ጭምር በሰለለበት ተግባር ሰበብ ተዓማኒነት እያጣ ሄዶዋል። ይህን ተከትሎ የመረጃ አጠባበቅ በዘመናዊ ዘዴ ተሻሽሎ ሊቀርብ እንደሚገባ ትርዒቱን ከብሪታንያዊው አቻቸው ዴቪድ ካምረን ጋ ባንድነት የከፈቱት የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል አሳስበዋል።

ሄንሪክ በመ/ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic