1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመረጃ ልዉዉጥና ጋብቻ በአፋር

ሐሙስ፣ መጋቢት 1 2003

አለም በግሎባላይዜሽን ተዉጦ፤ አንድ አገር መለያ መገለጫ ትዉፊቱን እንዳያጣ ባህልን ቋንቋን ጠብቆ ማቆየት ለአገር እድገት መሰረት መሆኑን ምሁር ይገልጻሉ።

https://p.dw.com/p/R7rq
ምስል AP

በአገራችን በተለይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትያትር ጥበባት ክፍል ተማሪዎች በማህበረሰብ ዉስጥ በመግባት የተለያዩ ማህበረሰቦች ያላቸዉን እሴት በማዉጣት በትያትር መልክ በማቅረባቸዉ ይታወቃሉ። ሰሞኑን በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ትያትር ጥበባት ክፍል ተማሪዎች የአፋር ብሄረሰብ የጋብቻ ስነ-ስርአትን በተመለከተ ትዉፊታዊ ድራማ ለተቋሙ መምህራን እና ተማሪዎች አቀርበዋል። የአፋር ባህልን በተለይም ባህላዊዉን የጋብቻን ስነ-ስርአትን በተመለከተ ጥናት ያደረገችዉ የአፋር ማህበረሰብ ተወላጅ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትያትር ጥበባት ክፍል የሶስተኛ አመት ተማሪ ፎዝያ ቢሩ የአፋር ማህበራሰብ የጋብቻ ስነ-ስነስርአት አብሱማ እንደሚባል ትገልጻለች። በዕለቱ ዝግጅታችን ስለ አብሱማ የጋብቻ ስነ-ስርአትና በአፍር ብሄረሰብ ዳጉ የተሰኘዉን ባህላዊ የመረጃ መለዋወጫ ስርአትን እናያለን።

ሙሉ ጥንቅሩን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ