የመምህራን እሥር በኮሬ ዞን
ሰኞ፣ ኅዳር 16 2017የመምህራን እሥር በኮሬ ዞን
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ በእሥር ላይ የሚገኙ ከ60 በላይ መምህራን በአስቸኳይ እንዲፈቱ የክልሉ መምህራን ማህበር ጠየቀ ፡፡ መምህራኑ ከባለፈው ረብዕ ጀምሮ በዞኑ ሳርማሌ ወረዳ ታሥረው የሚገኙት “ ደሞዛችን አለአግባብ ተቆርጦብናል “ በሚል ጥያቄ ካነሱ በኋላ ነው ፡፡ ደሞዛቸው በመቆረጡ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻችን ለመመገብ መቸገራቸውን ለዶቼ ቬለ የተናገሩ አንድ የወረዳው መምህር “ አቅም በማጣታችን የተነሳ አይደለም ቆመን ቁጭ ብለን ማስተማር ተስኖናል “ ብለዋል ፡፡የቀጠለው የሃድያ ዞን መምህራን አቤቱታ
ነሐሴ ወር አንስቶ የእሳቸውን ጨምሮ የመምህራን ደሞዝ ለልማት በሚል እየተቆረጠባቸው እንደሚገኙ ይናገራሉ ፡፡ ፡፡ በማያውቁትና ሁኔታ ደሞዛቸው በመቆረጡ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለመመገብ መቸገራቸውን ለዶቼ ቬለ የተናገሩት መምህሩ “ አሁን ላይ አቅም በማጣታችን የተነሳ አይደለም ቆመን ቁጭ ብለን ማስተማር ተስኖናል “ ይላሉ ፡፡
የእሥሩ መነሻ ክንያት
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ መምህራን አለ አግባብ ተቆርጦብናል ያሉት ደሞዛቸው እንዲመለስ ጥያቄ ማቅረባቸውን መምህራኑ ይናገራሉ ፡፡ እሳቸውና ባለቤታቸው በመምህርነት ሙያ ውስጥ እንደሚገኙ የጠቀሱትና የዚሁ ወረዳ ነዋሪ ብዙነሽ ሸመሮ “ ከባለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ በማያውቁት ሁኔታ ከደሞዛቸው 25 በመቶ ያህል እየተቆረጠ ይገኛል “ ብለዋል ፡፡በደቡብ ኢትዮጵያ ምክር ቤት ጉባኤ ውይይት የተደረገበት የመምህራን ደሞዝ አለመከፈል
የደሞዝ ቆረጣው አግባብ አለመሆኑን ፊርማ በማሰባሰብ አቤቱታ ማቅረባቸውን የጠቀሱት መምህርቷ “ ነገር ግን ይህን ተከትሎ እሥር ፣ ወከባ እና ደብድባ ነው የተፈጸምብን ፡፡ የእሥር ድርጊቱ እየተፈጸመ የሚገኘው ከባለፈው ረብዕ ጀምሮ ነው ፡፡ መጀመሪያ ላይ እኔና ባለቤቴ ከታሠርን በኋላ እኔን ዓርብ ዕለት ሲለቁኝ ባለቤቴ ግን እስከአሁን ከሌሎች 66 መምህራን ጋር እንደታሠረ ይገኛል “ ብለዋል ፡፡የደሞዝ ጭማሪ እና የመምህራን ቅሬታ
የማህበሩ ጥሪ
ዶቼ ቬለ በመምህራኑ ጉዳዩ ላይ የጠየቃቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኀበር ፕሬዚዳንት አማኑኤል ጳውሎስ የመምህራኑ ጥያቄ ተገቢና ትክክለኛ ነው ይላሉ ፡፡
አሁን ላይ በወረዳው 66 መምህራን ታሥረው እንደሚገኙ ማረጋገጫ የሰጡት የማህበሩ ፕሬዝዳንት “ በእሥር ላይ የሚገኙት መምህራን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ማህበሩ ከሚመለከታቸው የክልል አካላት ጋር እየተነጋገረ ይገኛል ፡፡እንዲሁም እሥር ፣ ድብደባና እንግልት ያደረሱ የፀጥታ አባላት በህግ እንዲጠየቁ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጥያቄ አቅርበን እየተከታተልን እንገኛለን “ ብለዋል ፡፡
ዶቼ ቬለ በመምህራኑ ላይ ተፈጽሟል በተባለው እሥርና አቤቱታ የወረዳ ፣ የዞንና የክልል አመራሮችን ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም ሃላፊዎቹ ለምላሹ ተባባሪ ባለመሆናቸው አስተያየታቸውን ማካተት አልተቻለም ፡፡
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ፀሐይ ጫኔ