የመልካም አስተዳደር እጦት በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 10.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የመልካም አስተዳደር እጦት በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ባለፈዉ ዓመት ማብቅያ ላይ ባካሄደዉ ጉባዔ የአመራሩ ዋነኛ ችግር የመልካም አስተዳደር እጦት መሆኑን አስታዉቆ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 32:13

የመልካም አስተዳደር እጦት በኢትዮጵያ

ኢህአዴግ የሚመራዉ መንግስት መስከረም ማብቂያ ላይ እንደተመሠረተም ይህንኑ ችግር ለማስወገድ በየመስኩ እንደሚጥር ቃል ገብቶአል። በመሠረቱ የመልካም አስተዳደር እጦት በተለያዩ ሃገራት እንደሚታወቀዉ የዴሞክራሲ፤ የሰብዓዊ መብት፤ የመናገርና የመሰብሰብ መብት የፕሪስ ነጻነት ከመሳሰሉት ጋር የተያያዘ ነዉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የመልካም አስተዳደር ችግር መኖሩን ተቀብሎ ለማስወገድ እንደሚጥር ቃል ሲገባ በአብዛኛዉ ማቃለል ላይ ያተኮረ እንደሚመስል መንግሥት የሚቆጣጠራቸዉ መገናኛ ብዙኃን ከሚያሰራጨቸዉ ዘገባዎች መረዳት ይቻላል። በዚህም አለበዚያ መንግሥት የመልካም አስተዳደር እጦትን ለማስወገድ ቃል ከገባ 6ተኛ ወሩን አገባዶአል። በዚህ ጊዜያት ዉስጥ በየአካባቢዉ በተለይ ደግሞ በኦሮሚያ ክልልና በአማራ አንዳንድ ወረዳዎች ተቃዎሞዎችና ግጭቶች መነሳታቸዉን አስተዉለናል። መንግሥት የችግሩን መንስዔ የመልካም አስተዳደር እጦት መሆኑን ቢያሳዉቅም በአገሪቱ ውስጥ ግጭቶች የተከሰቱት በዋናነት የአስተሳሰብ ብዝኃነት በመታፈኑ ነው ፍትህ በመጓደሉ ነዉ የሚሉ ነዋሪዎች ጥቂት አይደሉም። በኢትዮጵያ የመልካም አስተዳደር ችግርና በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩት ተቃዉሞዎች የዛሬዉ እንወያይ ትኩረት ነዉ።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic