የመላዉ ኢትዮጽያ አንድነት ድርጅት መኢአድ መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 18.07.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የመላዉ ኢትዮጽያ አንድነት ድርጅት መኢአድ መግለጫ

የመላዉ ኢትዮጽያ አንድነት ድርጅት መኢአድ በድርጅቱ ላይ በተካሄደ ጸረ መኢአድ እንቅስቃሴ እና በስራ አመራሩ መካከል የተፈጠረዉን ዉዝግብ እንደፈታ ትናንት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቋል።

default

በሌላ በኩል ህዝብ በአገር ዉስጥ እየተራበ እና እየተቸገረ የህዝብና የአገርን ሃብት ምዝበራ መቀጠሉ በጥብቅ እንደሚያወግም መግለጹ ተነግሮአል። በአገሪቱ ላለዉ አጠቃላይ ችግር ኤሃዴግ የፖለቲካ መፍትሄ ከመዉሰድ ይልቅ የተለያዩ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን በሽብርተኝነት በመፍረጅ ህዝብን እያሸማቀቀ ያለበትን ሁኔታ መኢአድ አጥብቆ እንደሚቃወም ማስታወቁን ታደሰ እንግዳዉ ከአዲስ አበባ የላከልን ዘገባ ያሳያል።

ታደሰ እንግዳዉ

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic