« የመላዉ አፍሪቃ የሙዚቃ ሽልማት» አሸናፊ | ኢትዮጵያ | DW | 19.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

« የመላዉ አፍሪቃ የሙዚቃ ሽልማት» አሸናፊ

በ 33 ዘርፎች በተካሄደ ዉድድር ድምጻዊት ሐመልማል አባተ «በአፍሪካ ባህላዊ የሙዚቃ ዘርፍ »አሸናፊ ሆናለች። የመላዉ አፍሪቃ የሙዚቃ ሽልማት በምህፃሩ  /AFRIMA/  አፍሪቃዊ የሙዚቃ ባለሙያወችን  አወዳድሮ መሸለም ከያዘ አራት አመታትን አስቆጥሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:54

« የመላዉ አፍሪቃ የሙዚቃ ሽልማት» አሸናፊ

 ይህ አመታዊ የሙዚቃ ሽልማት በ 33 ዘርፎች እጩወችን ሲመለምል ቆይቶ  ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ/ም ለአሸናፊዎች ሽልማት ሰጥቷል። በናይጄሪያ ዋና ከተማ ሌጎስ በተካሄደዉ በዚህ አራተኛዉ ዓመታዊ የሙዚቃ ሽልማት፤  አንጋፋዋን ድምጻዊት ሐመልማል አባተን ጨምሮ  ወይና ወንድወሰን፣ ክብሮም ብርሃነ፣ ሄኖክ መሀሪ እና ስንሻዉ ለገሰ በተለያዩ ዘርፎች ኢትዮጵያን ወክለዉ በዘንድሮዉ ዓመት የተወዳደሩ ድምጻዉያን ናቸዉ።  ከነዚህ መካከል ድምጻዊት ሀመልማል አባተ «በአፍሪካ ባህላዊ የሚዚቃ ዘርፍ »አሸናፊ ሆናለች።።

ፀሓይ ጫኔ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic