የመለስ የለንደን ጉብኝት እና የኢትዮጽያዉያን ተቃዉሞ | ኢትዮጵያ | DW | 31.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የመለስ የለንደን ጉብኝት እና የኢትዮጽያዉያን ተቃዉሞ

ብሪታንያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የአኢትዮጽያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከብሪታንያ አቻቸዉ ጎርደን ብራዉን ጋር በሁለቱ አገራት ግንኙነት በተለይ ደግሞ በአለም አቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ላይ ለመወያየት ዛሪ ለንደን ላይ ቀጠሮ አላቸዉ።

default

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ እና ጎርደን ብራዉን ዉይይታቸዉን ያደርጉበታል ተብሎ ከሚጠበቀዉ ከጎርደን ብራዉን ጽፈት ቤት ፊት ለፊት እዝያዉ ብሪታንያ የሚኖሩ ኢትዮጽያዉያን ከጠዋት ጀምሮ ተሰልፈዉ ተቃዉሞአቸዉን እያሰሙ ነዉ በስፍራዉ የሚገኘዉን ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህን ሂሩት መለሰ ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት አነጋግራዉ ነበር