የሕፃናት ጤና የአፍሪቃ ጉባኤ | ኢትዮጵያ | DW | 18.01.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሕፃናት ጤና የአፍሪቃ ጉባኤ

ከ3,5 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት አፍሪቃ ዉስጥ ወባን ጨምሮ ለመከላከል በሚቻሉ በሽታዎች በየዓመቱ ህይወታቸዉ ያልፋል። አዲስ አበባ በአፍሪቃ ኅብረት አዳራሽ ለሶስት ቀናት የተካሄደዉ የጨቅላ ሕፃናትን ሞት ማስቀረት ላይ ያተኮረዉ ጉባኤ ሀገራቱ ችግሩን ለማስወገድ በጋራ ለማከናወን የተስማቡበትን አቋም በማሳለፍ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

default

ከዚህ ሌላ ጉባኤዉ ለሕፃናት ስለሚያስፈልገዉ የተመጣጠነ ምግብ፤ በሕፃናት ላይ ስለሚፈፀሙ አጓጉል ልማዶችና ድርጊቶችንም በማንሳት ተወያይቷል። ኢትዮጵያ በነጋ እድሜያቸዉ የሚሞቱ ሕፃናትን ቁጥር መቀነስ እንደተሳካላትና ተሞክሮዋንም ማጋራቷ ተገልጿል። ኢትዮጵያ በወቅቱ የአፍሪቃ ሀገሮችን ለማነቃቃትና ለማበረታታት ኃላፊነት ወስዳ የተመለሰች ሲሆን በዚሁ መሠረት ጉባኤዉ ሲካሄድ የየሀገራቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሮችን በመጋበዝ ቃል ለማስገባት አዲስ አበባ ላይ መካሄዱንም አመልክተዋል።

ጉባኤዉ ላይ እስከትናንትና ድረስ የ27 የአፍሪቃ ሀገራት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሮች እንዲሁም በህፃናት ጤና ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎቻቸዉን የላኩ በጥቅሉ ሃምሳ የሚሆኑ የአፍሪቃ ሀገሮች ተገኝተዋል። የተመድ እስከ ጎርጎሮሳዊዉ 2015ዓ,ም በሁለት ሶስተኛ መቀነስን በአምዓቱ ግብነት ይዟል። ባለፈዉ ዓመት በብሄራዊ ደረጃ የተካሄደዉ የስነህዝብና ጤና ዳሰሳ ጥናት ዉጤት ኢትዮጵያ ከሚወለዱ አንድ ሺህ ህፃናት መካከል በዓመት አምስተኛ ዓመታቸዉን ሳያከብሩ ህይወታቸዉ ያልፍ የነበረ 217 ሕፃናት ቁጥር ወደ88 ዝቅ ማለቱን አመልክቷል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic