የሕፃናት የጉልበት ብዝበዛ ይገታ | ዓለም | DW | 12.06.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሕፃናት የጉልበት ብዝበዛ ይገታ

የተመድ ዓለም ዓቀፍ የሰራተኛ ድርጅት ILO የፋይናንስ ቀዉሱ በአጠቃላይ ሕፃናትን፤ ከምንም በላይ ደግሞ፤ ታዳጊ ሴቶችን ለከፋ የጉልበት ብዝበዛ ሳይዳርግ እንደማይቀር ከወዲሁ አሳሰበ።

default

...በህንድ ታዳጊዋ በሥራ ላይ...

አዝማምያዉም የሕፃናትን የጉልበት ብዝበዛ ለመግታት ላለፉት አስርት ዓመታት የተደረገዉን ጥረት ሊያስተጓጉል እንደሚችል ድርጅቱ በህፃናት ላይ የሚፈፀመዉን የጉልበት ብዝበዛ የሚቃወምበት ዓለም ዓቀፍ ዕለት ታስቦ የሚዉልበትን የዛሬዉን ቀን አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል። ለዘጠነኛ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ታስቦ በሚዉለዉ በዚህ ዕለት ILO ለታዳጊ ሴቶች እድል ይሰጣቸዉ የሚል መፈክር አስተጋብቷል።

አዜብ ታደሰ/ሸዋዬ ለገሠ