የሕግ በላይነት እጦትና የፖለትካ ቀዉስ በኢትዮጵያ  | ኢትዮጵያ | DW | 27.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሕግ በላይነት እጦትና የፖለትካ ቀዉስ በኢትዮጵያ 

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሌሎች የገዢዉ ፓርቲ  የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን፤  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሱት ጥያቄ ባለፈዉ ሰኞ መልስ እና ማብራሪያ መስጠታቸዉ ተዘግቧል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:04

የፖለትካ ቀዉስ በኢትዮጵያ 

በኢትዮጵያ ዉስጥ እየታየ ሥላለዉ የፖለትካ ቀዉስ እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ማብራሪያ እንዲሰጧቸዉ ጠይቀዉ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ያቀረቡት ጥያቄዎች አሁን እየተካሔደ ያለዉን የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ እንደሚያቀርቡ፣ ከዛ የሚደርሱበትን ነጥቦች ይዞዉ እንደሚመለሱ ለአባላቶቹ አስታዉቀዉ ነበር።

ጠ/ሚ ኃይለማርያም  የአራቱ የገዢዉ ግንባር ኢሕአዴግ አባል ከሆኑት (ኦሕዴድ፣ ህወሓት፣ ደኢሕዴንና ብኣዴን) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር  ባለፈዉ ሰኞ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመቅረብ ለጥያቄያቸው መልስ መስጠታቸዉ እየተዘገበ ነዉ።

የምክር ቤቱ አባላቶች ጥያቄያቸዉን ለጠ/ሚ ኃይለማርያም መጀመርያ ማቅረብ የፈለጉት በመደበኛ ስብሰባዉ አኳሃን ሳይሆን በተወከሉበት ድርጅቶች አኳሃን መሆኑ የፓርላማ አባል የሆኑት ምንጭ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። መንግስት እንደ መንግስት በኦሮሚያና በኢትዮጵ-ሶማሊ ክልሎች ድንበር ላይ የተከሰተዉን ግጭት ጨምሮ ሌሎችንም ማስቆም ለምን አልቻለም የሚለዉ ጥያቄ እንደቀረበላቸዉ ምንጩ ይናገራሉ።

የተከሰተዉ ችግርም የራሳቸዉ የከፍተኛ አመራር ድክመት መሆኑን እንደተቀበሉምና በዚህም ጉዳይ ላይ የኢሕአዴግ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይም ሒስ እያደረጉበት መሆኑን ጨምሮ አክሎበታል።

በንድፈ ሐሳብ ደረጃ ጠ/ሚ ኃይለማርያም በፓርላማ የተሾሙ በመሆናቸዉ ፓርላማዉ በፈለገዉ ጉዳይ ላይ ጠ/ሚንስትሩን ጠርቶ ማብራሪያ እንዲሰጡት  የመጠየቅ ስልጣን እንዳለዉ የመድረከ ምክትል ሊቀመነበርና የዉጭ ጉዳይዮች አላፍ ፕሮፌሴር በየነ ጰጥሮስ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

በአገርቱ ዉስጥ የነበረዉ የፖለትካ ቀዉስ፣ ግድያዉ፣ እስራቱ፣ መቁሰሉና ሰዎች ከቀያቸዉ መፈናቀላቸዉ አሁን ካለዉ ፖለትካዊና ማህበራዊ ቀዉስ ጋር በመዳመር «ዋንጫዉ ሞልቶ እንዲፈስ አድርጎታል» ሲሉ ፕሮፌሶር በየነ ይደመድማሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ የሚመለከታቸዉን የመንግስትም ሆነ የድርጅት አመራሮች ለማናገር ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic