የሕገ ወጥ የጫት ነጋዴዎች ክስ በዩኤስ አሜሪካ | ዓለም | DW | 19.04.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሕገ ወጥ የጫት ነጋዴዎች ክስ በዩኤስ አሜሪካ

አሥራ ሶስት የሶማልያና የየመን ተወላጅ የሆኑ አሜሪካውያን ጫትን በህገወጥ መንገድ ወደ ዩኤስ አሜሪካ አስገብተዋል በሚል በሀገሪቱ ፌዴራዊ ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው።

default

ተከሳሾቹ ባለፉት ስድስት ዓመታት ብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ዶላር ያስገኘ ጫት ማዛዋወራቸውን የክሱ መዝገብ አመልክቶዋል። የህግ ባለሞያና ጠበቃዉ ዶክተር ፍፁም አቻሜለህ ፊደራሉ ህግ ላይ በወንጀልነት የተጠቀሰዉ ይላሉ « በፊደራሉ ህግ የተፃፈዉ ጫት ዉስጥ ስላሉ ንጥረ ነገሮች ነዉ። አንደኛዉ ካቲኖን የተባለ ንጥረ ነገር ሲሆን ፣ ሁለተኛዉ ደግሞ ካቲን የተባለ ንጥረ ነገር ነዉ ያለዉ ጫት። ካቲኖን የሚገኘዉ ጫት ከተቆረጠ 48 ሰዓት ያልሞላዉ እርጥብ ጫት ዉስጥ ነዉ። በአሜሪካ ዉስጥ እርጥብ ጫት ይዞ መገኘት ከአንድ ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከባድ ወንጀል ነዉ።»

አበበ ፈለቀ

አርያም ትክሌ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic