የሕዳሴ ግድብ ጥናት | ኢትዮጵያ | DW | 18.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሕዳሴ ግድብ ጥናት

ግንባታ፣ በዉሃ ኮታ፣ በአካባቢዉ ተፈጥሮ፣ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚኖረዉን ተፅዕኖ እንዲያጠኑ ባለፈዉ ጥር ወር ለአርቴሊያ እና ብኣርኤል ለተባሉት ሁለት የፈረንሳይ ኩባንያዎች ኃላፊነት ተሰጥቶ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:02

ግድብ ጥናት

ኩባንያዎቹ ይህን ጥናት ቀጥለዉ እንዲሄዱበት ከኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን፣ የተዋቀረዉ የሦስትዮሹ ቴክኒካል ኮሚቴ የመጨረሻ ፊርማ አዲስ አበባ ሊፈረም እንደሆነ የግብፅ የዉኃ ሃብትና የመስኖ ሚንስትር ሞሃመድ አብደል አቲ መናገራቸዉ ተዘግቧል።


የግድቡን ተፅዕኖ ለማጥናት ዉሉን የተረከቡት ሁለቱም የፈረንሳይ ኩባንያዎች እና ቴክኒካል ኮሚቴዉ የሚፈራረሙት የመጨረሻ ስምምነት ለመፈራረም ዝግጅት ላይ እንዳሉ አቶ ብዙነህ ቶልቻ የኢትዮጵያ የዉኃ፣ የመስኖና ኢነርጂ ሚኒስትቴር የሕዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ይናገራሉ።

ሁለቱም የፈረንሳይ ኩባንያዎች እና ቴክኒካል ኮሚቴዉ ስምምነቱን የሚፈራረሙበት ቀነ ገደብ ይህ ነዉ ማለት አይቻልም ስሉ አቶ ብዙነህ ያብራራሉ።

ጥናቱን ለመጀመር ሦስቱም አገሮች ጥናቱን ከሚያካሂዱት ጋርም ግኑኙነት እያደረጉ እንደሆነዉ ያስረዳሉ።


ከሁለት ዓመት በፊት የሦስቱም አገራት ቴክኒካል ኮሚቴ ግድቡ በዉኃ ኮታ፣ በአከባብ ተፈጥሮ ላይ የሚያስከትለዉን፤ እንዲሁም ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ተፅዕኖዉን ለማጥናት ተስማምተዉ እንደነበር ተዘግቧል። ከሱዳን ድንበር 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘዉ ይህ ግድብ 74 ሚልዮን ኪዩ ቢክ ሜትር ዉኃ የመያዝ አቅም እንዳለዉ እና 6,000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎም ይጠበቃል።


የሦስቱም አገሮች መሪዎች፣ ሩዋንዳ ላይ ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀናት ከተሄደዉ የአፍሪቃ ኅብረት ጉባኤ በስተጎን ግድቡን በሚመለከት እንደሚነጋገሩ ዘገባዎች አመልክተዋል። ይሁን እንጂ አቶ ብዙነህ ኪጋሊ ላይ የተፋሰሱ አገሮች ዓመታዊ ስብስባ እንዳለጠቁመዉ፣ ትናንትም ይሁን ዛሬ መሪዎቹ ዉይይት ስለማድረጋቸዉ መረጃ እንደሌላቸዉ ተናግረዋል።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች