ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በአዲስ አበባ የቤቶች ፈረሳ በቅጽበት ቤት አልባ ያደረጋቸው ነዋሪዎችን በእንባ አራጭቷል፤ ሕጻናት ተማሪዎች፤ እናቶችና አረጋውያንንም ለጎዳና መዳረጉ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ ተጠቃሚዎች አነጋጋሪ ሆኗል ። የከተማዪቱ ከንቲባ «ከፍተኛ ፍልሰት»ን «መንግሥትን በመጣል በኃይል ሥልጣን» ከመቆጣጠር ጋር አያይዘው መናገራቸው በርካቶችን አስቆጥቷል ።
ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ እውቅና ያላቸው እናት እና ባልደራስ የተባሉ ሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ እንዳይችሉ መከልከላቸውን አስታውቀዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሁለቱም ፓርቲዎች ጉባኤዎች ላይ ታዛቢዎችን በመላክ ስብሰባውን ለመከታተል ሞክሮ እንደነበር ፓርቲዎቹ ገልፀዋል።
ትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግሥት አመሰራረት ላይ እምነት እንደሌላቸው ሦስት ፓርቲዎች ተናገሩ።
በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ዘርፈ ብዙ ጥቃትና ማህበራዊ ጫናዎች እንዲሻሻሉ ረጂም ርቀት መጓዝ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡ በኢትዮጵያ የህግባለሙያ ሴቶች ማህበር የህግ ድጋፍ አስተባባሪ ሀና ኃይለመለኮት በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት፤ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች አሁንም በአሳሳቢነታቸው ቀጥለዋል፡፡