የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ መራዘም | ኢትዮጵያ | DW | 28.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ መራዘም

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የሕዝብና ቤት ቆጠራ መራዘሙን ተቃወመ። የትግራይ ክልል ውሳኔው የመንግሥት የማስፈፀም አቅሙ ደካማ መሆኑ ያሳያል ብሎታል። የሕዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን የተላለፈበትን ምክንያት ይፋ ባደረገው መግለጫ፣ በግጭቶች ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደየነበሩበት ሳይመለሱ ቆጠራውን ማካሄድ እንደማይቻል ማመልከቱ ይታወሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:15

የትግራይ ክልል መራዘሙን ተቃውሟል

በተደጋጋሚ እየተራዘመ መካሄድ ከነበረበት ግዜ ሁለት ዓመት ያለፈው የሕዝብና ቤት ቆጠራ በያዝነው ወር መጋቢት 29 ሊካሄድ ዕቅድ ወጥቶለት በዝግጅት ሂደት ላይ ከቆየ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ላልተወሰነ ግዜ እንዲተላለፍ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል።  በጉዳዩ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየቀረቡ ሲሆን የትግራይ ክልል መንግሥት የአስፈፃሚውን አካል ውሳኔ ተቃውሞታል። የሕዝብና ቤት ቆጠራን አስመልክቶ የተላለፈውን የውሳኔ ሀሳብ መግለጫ የሰጡት የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድርና የንግድ፣ ኢንዳስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሐላፊ ዶክተር አብረሃም ተኸስተ ቆጠራው አለመካሄዱ የመንግሥትን የማስፈፀም አቅም ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው ብለዋል። እንዲሁም በሂደቱም የግልፅነት ችግር መኖሩን አክለው ገልፀዋል።በትግራይ ክልል በኩል ግን ቆጠራውን ለማካሄድ ሙሉ ዝግጁነት መኖሩን ዶክተር አብርሃም ተኸስተ ተናግረዋል፡፡ ይህን አስመልክቶ የሚመለከታቸው የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic