የሕዝብ ተወካዮች የ2012 በጀት አፀደቀ | ኢትዮጵያ | DW | 11.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

 የሕዝብ ተወካዮች የ2012 በጀት አፀደቀ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚቀጥለው ዓመት የቀረበው የ387 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት ረቂቅ ላይ ዛሬ ተወያየ። ባሳለፍነው ቅዳሜ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ በጀቱ ላይ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:43

ለ2012 የቀረበው በጀት ረቂቅ ላይ ውይይት ተደረገ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚቀጥለው ዓመት የቀረበው የ387 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት ረቂቅ ላይ ዛሬ ተወያየ። ባሳለፍነው ቅዳሜ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ በጀቱ ላይ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። የገንዘብ ሚንሥትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ዛሬ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የበጀት ዝርዝር ላይ ውይይት ተካሂዷል። ለ2012 ዓም የተያዘው በጀት ባለፈው ዓመት ከጸደቀው በጀት የ1 ነጥብ 6 ጭማሪ እንዳለው ሚንሥትሩ ተናግረዋል። ኢኮኖሚው በሚቀጥለው የበጀት ዓመት የተወሰነ መነቃቃት በማሳየት ከዘጠኝ በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ታሳቢ መደረጉንም አክለው ገልጠዋል። ዮሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። 

ዮሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic