1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕዝቦች መፈናቀል እና የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 25 2010

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየደረሱ ያሉ የሕዝቦች መፈናቀል እንዳሳሰበው ሰማያዊ ፓርቲ ገለጠ። በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂዞን ከደቡብ ክልል የጌዲዮ ዞን አዋሳኝ ወረዳዎች ከመቶሺ የሚልቁ፤ በቤንሻንጉልም በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በየአካባቢያቸው በተፈጠረ ግጭት ለመፈናቀል መዳረጋቸውን ፓርቲው አመልክቷል።

https://p.dw.com/p/2x7kC
Äthiopien PK Blue Party - Thema Vertriebene in Südäthiopien
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

«የተፈናቀሉ ሕዝቦች ሁኔታ ያሳስባል»

 የፓርቲው ኃላፊዎች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አክለውም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የዜጎች መታሰር መቀጠሉን ጠቅሰው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢል አህመድ ከአደባባይ ንግግር ባለፈ ለሕዝብ የገቡትን ቃል እንዲተገብሩ ጥሪ አቅርበዋል። መግለጫውን የተከታተለው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ