የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ዳግም መራዘም | ኢትዮጵያ | DW | 11.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ዳግም መራዘም

የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ዳግም መራዘም ከሚያስገኘው ጥቅም ይልቅ የሚያስከትላቸው እንቅፋቶች ይበዛሉ በማለት የውሳኔውን ተገቢ አለመሆን የኢዴፖ የቀድሞ ሊቀመንበር እና የምጣኔ ሃብት ባለሞያው አቶ ሙሼ ሰሙ ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናገሩ።

የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ዳግም መራዘም ከሚያስገኘው ጥቅም ይልቅ የሚያስከትላቸው እንቅፋቶች ይበዛሉ በማለት የውሳኔውን ተገቢ አለመሆን የኢዴፖ የቀድሞ ሊቀመንበር እና የምጣኔ ሃብት ባለሞያው አቶ ሙሼ ሰሙ ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናገሩ። ውሳኔው እንደ ሃገር ምንም ነገር ላይ መስማማት እንደማንችል ከማሳየቱም በላይ ሃገሪቱ የገደል አፋፍ ላይ ስለመሆኗ አመልካች ነው ብለዋል። አካሄዱ በቀጣዩ ዓመት የሚደረገው ሃገራዊ ምርጫ ስለመራዘሙም ሌላ ፍንጭ ሰጭ ሆኖ እንዳገኙትም አቶ ሙሼ ስጋታቸውን አመልክተዋል። ለዶይቸ ቬለ ሐሳባቸውን ያጋሩ ሁለት ሰዎች ደግሞ፦ ሕዝብ ተፈናቅሎ እና ጎዳና ላይ ሆኖ እያለ ይህ ውሳኔ መተላለፉ ፣ በሌላም በኩል በሃገሪቱ በመንግስታት መካከል ልዩነት በሰፋበት ሁኔታ ቆጠራው መራዘሙ ተገቢነቱ የማያጠራጥር ነው ብለዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች