የሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ | ኢትዮጵያ | DW | 28.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ

ረጅም ጊዜ የወሰደዉ ስብሰባ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።እዚያዉ መቀሌ የሚገኘዉ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ረዳት ፕሮፌሰር አቶ የማነ ዘርዓይ እንደሚሉት ግን ሕወሐት ዘመኑ የሚጠይቀዉን አመራር መስጠትና መፍጠር አልቻለም።

በኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግ ዉስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያደርጋል የሚባለዉ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ሊቀመንበሩን አቶ አባይ ወልዱን ከሊቀመንበርነት እና ከሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት ሻረ።መቀሌ-ትግራይ የተሰየመዉ የማዕከላዊ ከሚቴ ሥብሰባ የቀድሞዉን የፓርቲዉን ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤትን ወይዘሮq አዜብ መስፍንን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አግዷል።በሌሎች የፓርቲዉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ የተለያዩ እርምጃዎች መዉሰዱን አስታውቋልም።ረጅም ጊዜ የወሰደዉ ስብሰባ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።እዚያዉ መቀሌ የሚገኘዉ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ረዳት ፕሮፌሰር አቶ የማነ ዘርዓይ እንደሚሉት ግን ሕወሐት ዘመኑ የሚጠይቀዉን አመራር መስጠትና መፍጠር አልቻለም።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic