1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕወሃት መሪዎች ዉዝግብ እንደቀጠለ ነዉ

ሐሙስ፣ ኅዳር 19 2017

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት ጌታቸዉ ረዳ ባለፈዉ እሑድ በሰጡት መግለጫ የሚመሩት ቡድን ልዩነቱን በድርድር ለምፍታት ዝግጁ መሆኑን አስታዉቀዉ ነበር።ባለፈዉ ነሐሴ አጋማሽ በተደረገ ጉባኤ የፓርቲዉን የምክትል ሊቀመንበርነት ሥልጣን የያዙት አቶ አማኑኤል አሰፋ ትናንት በሰጡት መግለጫ ፓርቲዉን በሚመለከት ከዉጪ ወገኖች ጋር አንደራደርም ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4nXDb
አቶ አማኑኤል አሰፋ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ፓርቲዉን በሚመለከት ድርድር እንደማይደረግ አስታዉቀዋል
ከፊት ከግራ ወደቀኝ አቶ አማኑኤል አሰፋና ዶክተር ደብረ ፅዮን ገብረሚካኤል የሕወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በፓርቲዉ ጉባኤ ላይ ምስል Million Haileslasse/DW

የሕወሃት መሪዎች ዉዝግብ እንደቀጠለ ነዉ

የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕወሓት) ባለሥልጣናት የገጠሙት ፖለቲካዊ ዉዝግብ አሁንም እንቀጠለ ነዉ።የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሥልጣንን የያዙትና ያልያዙት የሕወሃት ባለሥልጣናት አንድ ከተማ ተቀምጠዉ በጋዜጣዊ መግለጫ የገጠሙት ንትርክ የክልሉን ሕዝብ ግራ እያጋባዉ ነዉ።የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት ጌታቸዉ ረዳ ባለፈዉ ዕሁድ በሰጡት መግለጫ የሚመሩት ቡድን ልዩነቱን በድርድር ለምፍታት ዝግጁ መሆኑን አስታዉቀዉ ነበር።ባለፈዉ ነሐሴ አጋማሽ በተደረገ ጉባኤ የፓርቲዉን የምክትል ሊቀመንበርነት ሥልጣን የያዙት አቶ አማኑኤል አሰፋ ትናንት በሰጡት መግለጫ ግን ፓርቲዉን በሚመለከት ከዉጪ ወገኖች ጋር አንደራደርም ብለዋል።

አቶ አማኑኤል አሰፋ በሰጡት መግለጫ ፥ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የህዝብ በጀት በማጭበርበር፣ በማባከን፣ ሕገመንግሥት በመጣስ ላይ ነው ሲሉ ኮንነዋል።አቶ አማኑኤል፣ ጌታቸው ረዳን "የቀድሞ ፕሬዝደንት" ብለው የጠርዋቸው ሲሆን፥ ለምን ተብሎ በጋዜጠኞች የቀረበላቸውን ጥያቄ ሲመልሱም ፓርቲያቸው ህወሓትን ወክለው ወደ ግዚያዊ አስተዳደሩ የገቡ ባለስልጣናት አስቀድሞ ውክልናቸው ማንሳቱ በመግለፅ፥ እርሳቸው ለመተካት ከፌደራል መንግስቱ ጋር ንግግሮች እየተደረጉ መሆኑ አመልክተዋል።

 

ህወሓት ለማፍረስ ያለመ እንቅስቃሴ በማድረግ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደርን የከሰሱት የህወሓቱ ከፍተኛ አመራር፥ በትግራይ ውስጥ እና ውጭ ወጣቶች በመመልመል፣ ስልጠና እና ገንዘብ በመስጠት በህወሓት ላይ አመፅ እንዲነሱ የማድረግ ተግባር በአስተዳደሩ ድጋፍና እውቅና እየተከወነ ነው ብለዋል።ህወሓት የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ኑሮ ለመመለስ ባለፈው ሳምንት የተጀመረው ሂደት እየሄደበት ያለው ሁኔታም ክፍተቶች ያሉት ነው ብሎ እንደማያምን አቶ አማኑኤል ጨምረው ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸዉ ባለፈዉ ዕሁድ በሰጡት መግለጫ መደራደር እንደሚፈልጉ አስታዉቀዉ ነበር
አቶ ጌታቸዉ ረዳ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት።ምስል Million Haileselassie/DW

 

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደርህወሓት በትግራይ የተለያዩ ወረዳዎች ያሉ ምክርቤቶች በመጠቀም  አስተዳዳሪዎች እያወረደ ነው፥ ይህም "መፈንቅለ መንግስት ነው" ሲሉ በተደጋጋሚ ሲገልፅ ይሰማል።ከሳምንታት በፊት በሃይማኖት መሪዎች አሸማጋይነት በቀጣይ በሚደረግ ውይይት ልዩነታቸው ለመፍታት ተስማምተዋል ተብለው የነበሩ ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች፥ ይህ ብዙም ሳይቆይ ወደቀድሞ ውዝግባቸው እና መወነጃጀል ተመልሰዋል።የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሳምንቱ መጀመርያ ሰጥተውት በነበረ ማብራርያ በዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን፥ ግዚያዊ አስተዳደሩ ስራው እንዳይከውን በማደናቀፍ እና ህዝቡ በመንግስት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ በመስራት መክሰሳቸው ይታወሳል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ፀሐይ ጫኔ