የሕንድና የፓኪስታን ዉዝግብ | ዓለም | DW | 26.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የሕንድና የፓኪስታን ዉዝግብ

ሕንድና ፓኪስታን የካሽሚር ግዛት ይገባኛል ዉዝግባቸዉ ዳግም መቀስቀሱ ተነገረ። የሕንድ መንግሥት የፓኪስታን የአየር ክልልን  በጦር ጄት ጥሶ በመግባት አንድ የአሸባሪዎች ማሰልጠኛ ቦታን በቦንብ መደብደቡን ገልፆአል። በሕንድ የጦር ጄቶች ቦንብ የተወረወረባቸዉ ኢላማዎች ሁሉ መዉደማቸዉንም አስታዉቋል።

ሕንድና ፓኪስታን የካሽሚር ግዛት ይገባኛል ዉዝግባቸዉ ዳግም መቀስቀሱ ተነገረ። የሕንድ መንግሥት የፓኪስታን የአየር ክልልን  በጦር ጄት ጥሶ በመግባት አንድ የአሸባሪዎች ማሰልጠኛ ቦታን በቦንብ መደብደቡን ገልፆአል። በሕንድ የጦር ጄቶች ቦንብ የተወረወረባቸዉ ኢላማዎች ሁሉ መዉደማቸዉንም አስታዉቋል። የሕንድ የመገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ በቦንብ ድብደባዉ ወደ 200 የሚሆኑ ሰዎች ተጎድተዋል፤ በርካቶች መሞተዋል። አንድ የሕንድ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፍተኛ ባለሥልጣን በበኩላቸዉ ሕንድ የአየር ድብደባዉን ያካሄደችዉ «የአጥፍቶ ጠፌ ጥቃት ይጣላል የሚል ስጋት በመድረሱ ነዉ»። ጥቂት ሰላማዊ ሰልፈኞች ፓኪስታንን በመቃወም ሕንድ መዲና ኒዉዴሊ ላይ ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል። ሰልፈኞቹ የሕንድ ገዥ ፓርቲ  የሆነዉን «ብሔራዊ አካሊ ዳል ፓርቲ» ን በመደገፍ ፓኪስታን ላይ ርምጃ እንዲወሰድ በመጮኽ ተቃዉሞአቸዉን አሰምተዋል።   ከሰልፈኞቹ መካከል አንዱ 
«የሀገራችን ጦር  ኃይል ዛሬ ያሳየዉ ማንኛዉም ከኛ ጋር ለመጋጨት የሚዳፈር ከባድ መከራ እንደሚገጥመው ነው። ቤታቸው ድረስ ዘልቀን እንመታቸዋለን።»     
የፓኪስታን የጦር ሠራዊት በበኩሉ የሕንድ የጦር ጀቶች በፓኪስታን አየር ክልል ገብተዉ የቦንብ ድብደባ ማድረሳቸዉን ቢያረጋግጥም በጥቃቱ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ነዉ ያስታወቀዉ።  እንድያም ሆኖ ፓኪስታን የአፃፈ መልስ እንደምትሰጥ መዛትዋ ተዘግቦአል። የአቶም ቦንብ ያላቸዉ ሕንድና ፓኪስታን የዛሬ አራት ዓመት የአየር ድብደባ ካካሄዱ ወዲህ የፓኪስታን መንግሥት ዛሬ የአስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ታዉቋል። በሂማላያ የሚገኘዉ የካሽሚር ግዛት ሕንድ ቻንይ እና ፓኪስታን የግዛት ግገባኛል ጥያቄ የሚወዛገቡበት ቦታ ነዉ።  

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ