የሐጂ ፀሎት | ዓለም | DW | 13.11.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሐጂ ፀሎት

ከኢትዮጵያም አራት ሺሕ አምስት መቶ ያሕል ምዕመናን ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል

default

የአሳማ ጉንፋን ወይም የH1 N1 ተሕዋስ ስርጭት ለዘንድሮዉ ሐጂ ወደ መካ የሚሔደዉን ምዕመን ቁጥር ይቀንሰዋል የሚል መላ ምት አስከትሏል።የስዑዲ አረቢያ መገናኛ ዘዴዎች ግን ተጓዡ ከወትሮዉ ብዙ አይቀንስም ባይ ናቸዉ።የሐገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ ላንዳድ ሐገራት ሐጃጆች ክትባት ለመስጠት ማቀዱም ተስምቷል።ባለፈዉ አመት በፖለቲካዊ ዉዝግብ ሰበብ ሐጂ ማድረግ ያልቻሉ ፍልስጤማዉያን ምዕመናን ዘንድሮ ተሳታፊዎች ናቸዉ።ከኢትዮጵያም አራት ሺሕ አምስት መቶ ያሕል ምዕመናን ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ ሐጃቾችን ለማጓጓዝ ከአዲስ አበባ -መዲና አዲስ በረራ ጀምሯል።የጂዳዉ ወኪላች ነብዩ ሲራክ ተጨማሪ ዘገባ አለዉ።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic