የሎው ሙቭመንት እና የፍቅረኛሞች ቀን | ባህል | DW | 20.02.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የሎው ሙቭመንት እና የፍቅረኛሞች ቀን

ባለፈው ቅዳሜ በአንዳንድ ፍቅረኛሞች ዘንድ የፍቅረኛሞች ቀን ወይም «ቫለንታይንስ ደይ» ተከብሎ ውሏል። በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ፤የሎው ሙቭመንት በሚል የተሰባሰቡ ወጣቶች ይህንን ቀን፤ ከፆታዊ ፍቅር መግለፃ ቀን ባሻገር፤ ሰዎች ለተቸገሩ በጎ ነገር የሚያደርጉበትም ቀን ሆኖ እንዲውል ወስኖ ተንቀሳቅሷል።

የሎው ሙቭመንት በመባል የሚጠራው የወጣቶች ስብስብ ፤ ባለፈው ሳምንት « be my yellow valentine » ሲል አንድ ጥሪ አድርጓል። አላማ እና ተግባሩ ግን ገና አልተጠናቀቀም። የፍቅረኛሞችን ቀን ምክንያት በማድረግ ፤ ሰዎች ቀኑ ለምን ይከበራል እያሉ ደገፉም አልደገፉም አንድ በጎ ነገር እንዲሰሩ የሎው ሙቭመንት ብለው የተሰባሰቡት ወጣቶች ተነስተዋል። ስለዚሁ እንቅስቃሴ፤ የዚሁ ስብስብ አባል እና አስተባባሪ የሆነችው በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የ4ኛ ዓመት የሕግ ተማሪ ረድኤት ከፍአለ ረድኤት ገልፃልናለች።

Hauptcampus der Universität Addis Abeba AAU

የሎው ሙቭመንት ድጋፍ ከሚያደርግላቸው የዮንቨርስቲ ተማሪዎች አንዱ ተሾመ ክንዴ ነው። የሕግ ተማሪ የነበረው ተሾመ፤ በወቅቱ በገጠመው የስነ ልቦና ችግር ምክንያት ትምህርቱን በአግባቡ ባለመከታተሉ እና ውጤቱ አነስተኛ በመሆኑ ትምህርቱን ለማቋረጥ ተገዶ ነበር። ወጣቱ አሁን የማህበራዊ ሳይንስ የማታ ተማሪ ነው።

ተሾመ ከገንዘብ በተጨማሪ ከልጅነቱ ጀምሮ የቆዳ መደራረብ ችግር እንዳለበት ገልፆልናል። የሎው ሙቭመንት የተለያዩ የስነ ልቦና፤ የሰውነት አስተዳደጋቸው ላይ ችግር የገጠማቸውን ተማሪዎች ይተባበራል። ሌላዋ ድጋፍ አግኚ ተማሪ ዝይን ትባላለች።እሷም ስለምታገኘው ድጋፍ ገልፃልናለች።

ወጣቶቹ እንደዚህ አይነት የአበባ ሽያጭ ሲያዘጋጁም ይህ የመጀመሪያቸው አልነበረም።ባለፈው ዓመት በአበባ ሽያጭ 42 000 ብር ለማሰባሰብ እና ሌሎችን ለመርዳት ችለዋል።በቅዳሜው የአበባ ሽያጭ አባል ከሆኑት 30 ወጣቶች በተጨማሪ፤ሌሎች በጎ ፍቃደኞችም የሎው ሙቭመንትን ተባብረዋል።

የሎው ሙቭመንት የወጣቶች ስብስብ እና ለሌሎች ፍቅራቸውን የገለፁበት እንቅስቃሴ ለመስማት ከፈለጉ የድምፅ ዘገባውን ይጫኑ።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic