የ«ልዩ ፖሊስ» ጥቃት በኦሮሚያ ወረዳዎች  | ኢትዮጵያ | DW | 28.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የ«ልዩ ፖሊስ» ጥቃት በኦሮሚያ ወረዳዎች 

ካለፉት ሦስት ወራት ወዲህ የሶማሌ ክልልን በሚያዋስኑ 14 የኦሮምያ ክልል ወረዳዎች አለመረጋጋት መታየቱ ታዉቋል። በአካባቢዉ ላይ በተለይ  «ልዩ ፖሊስ»  የተባሉት  የሶማሌ ክልል ታጣቂ ቡድኖች በተጠቀሱት ወረዳዎች ዉስጥ በመግባት በነዋሪዎች ላይ የኃይል ጥቃት መፈፀማቸዉ ንብረት ማዉደማቸዉ ተዘግቦአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:23

ልዩ ፖሊስ

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልን የሚያዋስኑ የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች ከታህሳስ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ  አለመረጋጋት ዉስጥ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችለዋል። «ልዩ ፖሊስ» በመባል የሚጠራዉና የሶማሌ ክልል ታጣቂ ኃይል መሆኑ የሚነገረዉ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙት 14 አዋሳኝ ወረዳዎች ዉስጥ ሰርጎ በመግባት በነዋሪዎች ላይ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ  ዘገባዎች  ያመለክታሉ። ከኢትዮጵያ ሶማሌ ተነሱ የተባለዉ እነዚህ «የታጠቁ ኃይሎች» በእነዚህ ወረዳዎች የሚፈፅሙት ጥቃት ምን ዓላማ አንግቦ ነዉ? በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፍ የሆኑት አቶ አዲሱ አራጋ ይህ ጥቃት የወሰንና የንብረት የላማ እንዳለዉ ይናገራሉ።

በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ቁምቢ ወረዳ ጥቃቱ እንደተጀመረና ከዛም በኋላ ወደ ጭናግሳን፣ ምዳጋ ቶላ፣ ጉርሱም፣ ማዩ ሙሉቄና ባብሌ ወረዳዎች መስፋፋቱን አቶ አዲሱ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። በዚህ ጥቃት የሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አቶ አዲሱ ተናግረዋዉ ለግዜዉ ግን ምን ያህል ሰዉ እንደተጎዳ  በቁጥር መረጃ የለኝም ብለዋል።

ሰሞኑን  በጉርሱም ወረዳ ይህ ግጭት መባባሱን የአከባቢዉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። የጭናግሳን ወረዳ ነዋሪ የሆኑት፣ ግን ስማቸዉ ለግዜዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉት ግለሰብ፣ ወረዳቸዉ ከጉርሱም ወረዳ ጋር እንደሚዋሰን ና በሁለቱም ወረዳዎች የሚፈፀሙ ጥቃቶች «በጣም አሳሳቢ» መሆኑን ተናግረዋል። ከባለፈዉ ሳምንት ጀምሮ በሁለቱም ወረዳዎች የመከላክያ ሰራዊት ሰፍሮ እንዳደሚገኝ የገለፁት እኚህ ነዋሪ  «በየእለቱ ሰዉ ሳይሞት የቀረበት ቀን የለም» ሲሉም አክለዉ ተናግረዋል።

«ወጥቶ መግባት አሁን አሰፈር ሆኖዋል። ተማርዎችም ሆኑ አስተማሪዎች ለነፍሳቸዉ ስለ ፈሩ ብዙ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ማስተማር አቁመዋል። ግጭቱ ከተባባሰ ከአንድ ወር ወዲህ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአከባብዉ ነዋሪዎች በዚህ ግጭት ህይወታቸዉን አጥተዋል።»

ለዚህ ግጭት መፍቴ ለመስጠት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ሆነ በእትዮጵያ ሶማሌ ክልል በኩል የተሰራ ስራ አለየሁም የሚሉት የጭናግሳን ወረደ ነዋሪ ግን ጉዳዩ ኮማንድ ፖስትን ይመለከታል መባሉን ሰምቻለዉ ይላሉ። አቶ አዲሱ ግን የክልል መንግስታት ሆኑ የፊደራል መንግስት ለዚህ ጉዳይ መፍቴ ለማምጣት ስምምነት አድርገዉ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ብለዋል።

«ልዩ ፖሊስ» የተሰኙት በሶማሌ ክልላዊ መንግስት እዉቅና እንደሚንቀሳቀሱና የክሉልም መንግስት ለዚህ ጥቃትተጠያቂ መሆን አለበት ሲሉም ቅሬታቸዉን የሚያሰሙ አሉ። አቶ አዲሱ ይህን እንዴት ይመለከቱታል?

ይህ ግጭት በምዕራብ ሃራርጌ ዞን ቦርዶዴ ወረዳ፥ በባሌ ዞን ደግሞ በዳዌ ሰረር፣ በሳዌና፣ በማዳ ዋላቡና ራይቱ ወረዳዎች፥ በጉጅ ዞን ጉሚ፣ ኤሌሎና ሊዮን ወረዳዎች፥ እንዲሁም በቦራና ዞን ሞያሌ ወረዳ ዉስጥም እንደምታይ አቶ አዲሱ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት በኩል ማብራርያ ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሰካም።


መርጋ ዮናስ 
አዜብ ታደሰ              

Audios and videos on the topic