የልማት ርዳታ ለኒዠር  | አፍሪቃ | DW | 21.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የልማት ርዳታ ለኒዠር 

ምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ኒዠር ዋነኛ የጀርመን እና የአውሮጳ ህብረት አጋር ናት።  ምክንያቱም በያመቱ ከ100,000 የሚበልጡ ስደተኞች በሜድትሬንያን ባህር በኩል ወደ አውሮጳ ለመግባት እያሉ  በኒዘር በኩል እያደረጉ ወደ ሊቢያ ወይም አልጀርያ ይጓዛሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:00

ኒዠር

ከዓለም ድሆች ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኒዠር ስልታዊ ትርጓሜ ከፍ እያለ ሄዷል። በዚሁ ሰበብም ጀርመን እና አውሮጳ ህብረት ከዚችው ሀገር ጋር ያለውን የልማት ትብብር ከፍ ለማድረግ አቅደዋል። የጀርመን የኤኮኖሚ ትብብር ሚንስትር ጌርድ ሚውለር ይህንን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ይበጃል ያሉትን የማርሻል እቅድ የተሰኘውን 30 ገፆች ያሉትን ዝርዝር አሰራሮች የሰፈሩበትን ሰነድ በሳምንቱ አጋማሽ ለሀገራቸው ምክር ቤት አቅርበዋል።  እቅዱ በተለይ ፍልሰትን የማስቀረት፣  ድህነትን የመታገል  እና ለአፍሪቃ  ወጣቶች አስተማማኝ የወደፊት ዕድል ፣ ማለትም፣ የስራ ቦታ የመፍጠር ዓላማዎችን ይዞ ቢነሳም፣  የአየር ንብረት ለውጥን መገደብ፣ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አጋርነትን እና ንግድን ማበረታታት ለሚሉትም ሀሳቦች  የተሰኙት ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረት አግኝተዋል። 


ይሁንና፣ በጀርመን ኤኮኖሚ ውስጥ የአፍሪቃን ጉዳይ የሚከታተለው ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ክርስቶፍ ካነንጊሰር  ሀሳቡ የሚደገፍ መሆኑን ቢገልጹም፣ የማርሻል እቅዱ በተግባር የሚተረጎምበት አሰራር ግልጽነት ይጎድለዋል ሲሉ ትችት ሰንዝረዋል።
« ይህ ሚንስትሩ ያሉት ሁሉ ትክክለኛ ነው። በተለይም  በአህጉሪቱ የግል ወረትን የማነቃቃቱ እና  የግል ብዑላን ታታሪነትን የማቃለሉ ሀሳብ።  እያንዳንዱ፣  በተጨባጭ ምን ማድረግ እንደሚፈልግ ሰፊ ውይይት ሊደረግበት ይገባል ብዬ አምናለሁ። የማርሻል እቅዱ አሁንም ግልፅ አይደለም። ስለዚህ የኤኮኖሚው ዘርፍ እቅዱን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ተጨባጭ ዘዴዎች እንዲቀርቡለት ይጠብቃል።»
የተለያዩ የአፍሪቃ ስልቶች መዘጋጀት በያዙበት ባሁኑ ጊዜ ፣ ጀርመን እና የአውሮጳ ህብረት ለኒዠር የሚሰጡትን የልማት ርዳታ አጠናክረው ቀጥለዋል። 
የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ባጠቃላይም የማርሻል እቅዶችን ስኬታማነት በጥርጣሬ ነው የሚመለከቱት። 
 

ሜርክል ባለፈው ጥቅምት ወር ኒዠርን በጎበኙበት ጊዜ ጀርመን ለዚችው ምዕራባዊት ሀገር የምትሰጠውን የልማት ርዳታ ወደ አውሮጳ የሚመጡትን ስደተኞች በማስቆሙ ተግባር ላይ ብቻ እንደማትወስነው ቃል ገብተው ነበር። 
« በኒዠር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተራቡ፡  ይህቺው  ምዕራብ አፍሪቃዊት  ሀገር  ሕገ ወጥ ስደተኞችን  የሚያጓጓዙትን ተሽከርካሪዎች  ብቻ  እንድታስቆም  ርዳታ  መስጠታችንን  ማንም ሊረዳው አይችልም። »

በዚህም የተነሳ መራሒተ መንግሥቷ ለኒዠር ተጨማሪ 17 ሚልዮን ዩሮ ለመስጠት  ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው። ገንዘቡን ኒዠርን የስራ ቦታ ለምትፈጥርበት እና ትምህርት ቤቶችን ለምትገነባበት ተግባር  እንድታውለው የታሰበ ነው።  ቀደም ሲል ከመራሒተ መንግሥቷ ሁለት ወር በፊት ኒዠርን የጎበኙት ጀርመናዊው የኤኮኖሚ ትብብር ሚንስትር ጌርድ ሚውለርም  15 ሚልዮን ዩሮ የልማት ርዳታ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ይኸው ርዳታም በተለይ ስደተኞች መተላለፊያ ባደረጉዋቸው የኒዠር ገጠር አካባቢ የስራ ቦታ ለመክፈቺያው ተግባር የሚውል ነው።  
« እርግጥ፡  የወጣቱን የወደፊት እድል ዋስትና ለማረጋገጥ  የስራ ቦታ መፍጠር  አስፈላጊ ነው። ይህን እውን ማድረግ  ትልቅ ፈተና ነው።  ነገር ግን፣ ጀርመን  ይህንኑ ለማሳካት ብዙ ልታደርገው የምትችል ነገር አለ።  ለምሳሌ፣  የጀርመን  የልማት ርዳታ ፣  በዚያው በአፍሪቃዊቱ  ሀገር ውስጥ  በሁለት  ቋንቋዎች  የሙያ ስልጠና በሚሰጥበት ተግባር ላይ ሊውል ይችላል። »

የስራ ቦታ፡ እንዲሁም፡ የሙያ ስልጠና መፍጠር የጀርመናውያኑ የልማት ትብብር ያተኮረበት ማዕከላይ ነጥብ ነወ። እርግጥ ይህ ፈጣኑን ስኬት አያስገኝም። ሚውለርም ሆኑ ሜርክል በገቡት ቃል መሰረት፡ እስካሁን በተጨባጭ የቀረበ ፕሮጀክት የለም። በአሁኑ ጊዜ ምን ዓይነት ፕሮጀክት የት እና እንዴት እንደሚጀምር እየተጣራ ነው።ጅመን ለኒዠር ሶስተኛ ትልቋ የልማት ርዳታ አቅራቢ ሀገር ናት። ከዚሁ ጎንም የአውሮጳ ህብረት በምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ግዙፍ የትብብር ስራ ጀምሯል።ባለፈው ታህሳስ  የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ፌዴሪካ ሞጌሪኒ ምን ያህል ገንዘብ ለኒዠር እንደሚሰጥ ገልጸዋል።


« የአውሮጳ ህብረት በኒዠር  540 ሚልዮን  ዩሮ የሚያወጡ  ዘጠኝ ፕሮጀክቶች ለመጀመር ቃል ገብቷል። ፕሮጀክቶቹ  በገጠሩ አካባቢ ልማት፡ በሙያ ስልጠናው እና ለወጣቱም የስራ ቦታ ፈጠራው ላይ ያተኩራል። »
እነዚህ ፕሮጀክቶች ኒዠርን ብቻ ሳይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ የአወሮጳውያኑንም ጥቅም ያስጠብቃሉ። በልማቱ ትብብር ርዳታ ምላሽ ኒዠር የሕገ ወጥ አፍሪቃውያን ስደተኞች ዝውውር ማብቃት፡ እንዲሁም፡ በሕገ ወጦቹ ሰው አሸጋጋሪዎች አንፃር ትግሏን ማጠናከር ይጠበቅባታል። ከዚህ በተጨማሪም ከሊቢያ ወደ ሜድትሬንያን የሚግዋዙ ስደተኞችን ያሳፈሩ ተሽከርካሪዎችን ጉቦ እየተቀበሉ እንዳላዩ በማየት በሚያሳልፉት በምግባረ ብልሹዎቹ ፖሊሶች ላይ ርምጃ መውሰድ ይኖርባታል።

በጦር መሳሪያ እና በአደንዛዥ ዕፅ ንግድ አንፃርም እስካሁን እያደረገችው ካለው በተሻለ መንገድ መታገል አለባት። አውሮጳውያን በአሁኑ ጊዜ ግልጽ ለማድረግ የሚፈልገው በኒዠር በጀመራቸው ፕሮጀክቶች አማካኝነት በዚችው ሀገር በኩል ወደ አውሮጳ የሚመጣው ስደተኛ ቁጥር መምጣታቸውን ነው። የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ፌዴሪካ ሞጌሪኒ በኩራት ነበር የገለጹት።
« በአሁኑ ጊዜ በኒዠር በኩል እያደረጉ ወደ አውሮጰ የሚመጡት ስደተኞች ቁጥር  በየወሩ 1,500  ነው። እንደሚታወቀው፣ ከኒዠር ጋር   የልማት ትብብራችንን  ከማስፋፋታችን ከጥቂት ወራት በፊት ፡ ቁጥሩ  70,000  ነበር።  »
የስደተኞቼ ቁጥር እንዴት ሊቀንስ መቻሉ በወቅቱ ግልጽ አይደለም። ስደተኞቹ ሌላ መተላለፊያ መንገድ እየተጠቀሙ  ይሁን አይሁን አይታወቅም። 
ይሁን እንጂ፣ አውሮጳውያኑ ቁጥሩ የቀነሰበትን ድርጊት ለኒዠር የሚሰጡት ብዙ ሚልዮን ዩሮ ርዳታ ትክክለኛ ነው በሚል እንደመከራከሪያ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።  ጥያቄው፣ በልማት ርዳታ ስም የሚላከው  ተጨማሪው ገንዘብ በርግጥ የስራ እና  የሙያ ስልጠና  ቦታ እየተፈጠረበት ፣ እንዲሁም ፣  ትምህርት ቤቶችም እየተገነቡበት የሚለው ነው። ይህን በተመለከተ እስካሁን የተመዘገበ አዎንታዊ ውጤት አልቀረበም።

አርያም ተክሌ/የንስ ቦርቸርስ

ልደት አበበ
   .
 

 

 

Audios and videos on the topic