የላፍቶ ነዋሪዎች አቤቱታ | ኢትዮጵያ | DW | 23.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የላፍቶ ነዋሪዎች አቤቱታ

ዘጠኝ ሺሕ አባዎራዎች እንደሚሆኑ የሚናገሩት ነዋሪዎች እንደሚሉት የክፍለ-ከተማዉ ባለሥልጣናት ለተለያዩ አገልግሎቶች ማሟያ በሚል በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ገንዘብ ሲቀበሏቸዉ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:58

የላፍቶ ነዋሪዎች አቤቱታ

ከአዲስ አበባ ነፋስ-ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚባለዉ አካባቢ ነዋሪዎች «ቤታችን ፈረሰ፤ መሬታችንንም ተቀማን» በማለት አቤት አሉ።ዘጠኝ ሺሕ አባዎራዎች እንደሚሆኑ የሚናገሩት ነዋሪዎች እንደሚሉት የክፍለ-ከተማዉ ባለሥልጣናት ለተለያዩ አገልግሎቶች ማሟያ በሚል በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ገንዘብ ሲቀበሏቸዉ ነበር።በቅርቡ ግን ቤታቸዉን እያፈረሱ ይዞታቸዉን ለሐብታሞች መስጠታቸዉን ነዋሪዎቹ አስታዉቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ እንደዘገበዉ «አቤት» ባዮቹ  አዲስ አበባ በሚገኘዉ በተቃዋሚዉ የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፅሕፈት ቤት ዉስጥ ተሰብስበዋል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic