የላይቤርያ አጠቃላይ ምርጫ | ኢትዮጵያ | DW | 08.10.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የላይቤርያ አጠቃላይ ምርጫ

ሁለት የምዕራብ አፍሪቃ ሀገሮች፡ ማለትም የካሜሩን እና የላይቤርያ ሕዝቦች በሚቀጥሉት አራት ቀናት ፕሬዚደንታዊ እና ምክር ቤታዊ ምርጫዎች ያካሄዳሉ። ካሜሩን ውስጥ ነገ እሁድ እአአ ጥቅምት ዘጠኝ ቀን 2011 ዓም በካሜሩን ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ይደረጋል።

default

የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ኤለን ጆንሰን

በካሜሩን ካለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት ወዲህ በስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚደንት ፖል ቢያ አዲሱ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ሆነው መመረጣቸው እንደማይቀር የፖለቲካ ታዛቢዎች ገልጸዋል። የሰባ ስምንት ዓመቱ ፕሬዚደንት ቢያ ለከፍተኛው የሀገር ስልጣን በተከታታይ አሁን በተከታታይ ለስድስተኛ ጊዜ ነው የሚወዳደሩት።
የፊታችን ማክስኞ ደግሞ እአአ ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓም በላይቤርያ ምክር ቤታዊ እና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ይካሄዳል። በአፍሪቃ የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ ብሄር የሆኑት የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ፕሬዚደታዊው ምርጫ ለማሸነፍ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ስልጣን በያዙበት ጊዜ የገቡትን ቃል አላሟሉም በሚል ቅር የተሰኘባቸውን ሕዝብ እምነት መልሰው ለማግኘት ብዙ ሞክረዋል። ይሳካላቸው መሆን አለመሆኑ የፊታችን ማክሰኞ ይለያል።

አርያም ተክሌ
መስፍን መኮንን

Audios and videos on the topic