የላይቤሪያ ፕሬዚደንት የኢትዮጵያ ጉብኝት | አፍሪቃ | DW | 28.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የላይቤሪያ ፕሬዚደንት የኢትዮጵያ ጉብኝት

የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ዛሬ በኢትዮጵያ የአራት ቀን ይፋ ጉብኝት ጀመሩ። ፕሬዚደንት ሰርሊፍ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ከፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እና ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በሀገሮቻቸው መካከል ስላለው ግንኙነት እና ስለአህጉራዊ ጉዳዮች ተወያይተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:10

ፕሬዚደንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ

ከውይይቱ በኋላ ፕሬዚደንት ሰርሊፍ  ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሰጡት በአፍሪቃው ያለውን የንግድ ልውውጥ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ  ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያምም በተመድ የፀጥታው  ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነ የሆነችው ኢትዮጵያ አፍሪቃን በሚመለከቱ፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ የአህጉሩን የጋራ ድምጽ እንደምታሰማ እና ከላይቤሪያም ጋር በቅርብ እንደምትሰራ አስታውቀዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ 


 

Audios and videos on the topic