የሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ የኢትዮጵያ ጉብኝት  | ዓለም | DW | 19.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ የኢትዮጵያ ጉብኝት 

ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ከአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ባለሥልጣናት እና ከአሜሪካን ኤምባሲ ሠራተኞች ጋር ይወያያሉ። ሆኖም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከዚህ ያለፈ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:21

የሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ

በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሬን ፊልድ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ከዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተሠራጨው መረጃ መሠረት ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ከአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ባለሥልጣናት እና ከአሜሪካን ኤምባሲ ሠራተኞች ጋር ይወያያሉ። ሆኖም ከዚህ የዘለለ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ዶቼ ቬለ የጠየቃቸው ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሥራ ኃላፊ ስለ ሚኒስትሯ ጉብኝት መረጃ እንደሌላቸው አስታውቀዋል። አንድ የአካባቢው የጂኦ ፖለቲካ ምሁር ግን ሚኒስትሯ ኢትዮጵያን የሚጎበኙት በኢትዮጵያ የረገበ የመሰለው አመጽ አሜሪካንን በእጅጉ ስለሚያሳስባት ነው ይላሉ። የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ አለው። 


መክብብ ሸዋ 


ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች