የሊቢያ ውዝግብ እና የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ምክክር | ዓለም | DW | 17.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሊቢያ ውዝግብ እና የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ምክክር

በሊቢያ የኮሎኔል ሙአመር ኧል ጋዳፊ ጦር ኃይላት በመንግስቱ አንጻር በሚታገሉት ዓማጽያን ላይ የጀመረውን የጥቃት ዘመቻ ማስቆም ይቻል ዘንድ የተመድ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ዛሬ በሊቢያ ላይ የበረራ ዕገዳ ማዕቀብ ባፋጣኝ እንዲጥል ፈረንሳይ፡ ብሪታንያ እና ዩኤስ አሜሪካ ከፍተኛ ጥረት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

default

ይህ በዚህ እንዳለ፡ የሊቢያ መንግስት ጦር ኃይላት በዓማጽያኑ አንጻር ጥቃታቸውን ማጠናከራቸው እና አንዳንድ በዓማጽያኑ እጅ የነበሩ ከተሞችን መልሰው መቆጣጠራቸው ተሰምቶዋል።

በሊቢያ የኮሎኔል ሙአመር ኧል ጋዳፊ ጦር ኃይላት በመንግስቱ አንጻር በሚታገሉት ዓማጽያን ላይ የጀመረውን የጥቃት ዘመቻ ማስቆም ይቻል ዘንድ የተመድ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ዛሬ በሊቢያ ላይ የበረራ ዕገዳ ማዕቀብ ባፋጣኝ እንዲጥል ፈረንሳይ፡ ብሪታንያ እና ዩኤስ አሜሪካ ከፍተኛ ጥረት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

Libyen Rebellen Widerstand


የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ትናንት በዝግ ባካሄደው ስብሰባው ላይ ብሪታንያ እና ሊባኖስ የበረራ ዕገዳ ማዕቀብ መጣል እንዲያስችል ባቀረቡት ረቂቅ ውሳኔ ላይ ተወያይቶዋል። ሊባኖስ ከዐረቡ ሊግ አባላት መካከል በሊቢያ ጋዳፊ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣልም የጠየቀች ብቸኛዋ ሀገር ናት።

በጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ውስጥ ብቸኛዋ ሀገር ናት። የረቂቁ ውሳኔ ደጋፊዎች ማዕቀቡ ትክክለኛ ርምጃ መሆኑን ሩስያ እና ቻይና የመሳሰሉትን ሀገሮች ማሳመን ሳይሳካላቸው ነበር የትናንቱ የምክር ቤቱ ስብሰባ ያበቃው። ጀርመን እና ኢጣልያን የመሳሰሉት የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራትም የበረራ ዕገዳ እንዲጣል የቀረበውን ሀሳብ አልደገፉትም። የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቬለ የበረራ ዕገዳ ማለት ወታደራዊ ርምጃ ነው በሚል ይህን ዓይነት ውሳኔ እንደማይትቀበል አስታውቀዋል።

« በእኛ እምነት ይህ አስቸጋሪ እና አደገኛ ነው። እና ካሁን በፊት ያልኩትን ነው አሁንም መድገም የምችለው። በሰሜን አፍሪቃ ውስጥ በሚጀመር ውጊያ ውስጥ መዘፈቅ አንፈልግም። »

በሽትራስቡርግ የሚገኘው የአውሮጳ ምክር ቤት እንደራሴዎችም ትናንት ባካሄዱት ምክክር ላይ ህብረቱ በጋዳፊ አንጻር ለሚታገሉት ዓማጽያን ተገቢውን ድጋፍ ያልሰጠበትን ድርጊት ወቅሰዋል። የጋዳፊ ጦር ኃይላት ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ ባጣናከሩት ዘመቻ በምስራቁ እና በምዕራብ ሊቢያ የሚገኙ በዓማጽያኑ ተይዘው የነበሩ ሚዙራታን፣ ብሬጋን እና ከቤንጋዚ በስተደቡብ ያለችውን አጃቢያን የመሳሰሉ ከተሞችን እንደገና መቆጣጠራቸውን እና ያማጽያኑ ጠንካራ ሰፈር የሆነችውን ቤንጋዚን ለመያዝ መቃረባቸውን የጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አል ኢዝላም ገልጸዋል።

Libyen Soldaten Panzer Gadhafi


« ውጊያው በአርባ ስምንት ሰዓት ውስጥ ያበቃል። የጦር ኃይላችን ቤንጋዚ መዳረሻ ላይ ነው የሚገኘው። የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ምንም ዓይነት ውሳኔ ቢያሳልፍ፡ በጣም ዘግይቶዋል።

በሰሞኑ ውጊያ ቢያንስ ሀያ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን አንድ ሀኪም ገልጸዋል።

እርግጥ፡ ተስፋ ያልቆረጠው የቤንጋዚ ህዝብ ትግሉን እንደማያቋርጥ አስታውቋል። ይሁንና፡ ቀላል እንደማይሆን አላጣውም።

«ምንም አንፈራም። ምክንያቱም ሞት አንድ ጊዜ ነው። እና ጋዳፊ እንደገና እንዲጨቁኑን አንፈልግም። እንደገና በጋዳፊ ከመመራት አዎ ሞት ይሻላል። »

በዚህ ፈንታ በጋዳፊ ላይ ፖለቲካዊ ግፊት ማሳረፉ ብሎም በአንጻራቸው ማዕቀቡ እንዲጠናከር፡ የተመድ ጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤትም ተመሳሳይ ርምጃ እንዲወስድ የተሻለ እንደሚሆን እንደምፈልጉ ገልጸዋል።

« የጋዳፊን የመንግስት አውታር የገንዘብ ምንጭን በተቻለ መጠን ማድረቅ እንፈልጋለን። መንግስቱ በህዝቡ አንጻር ጦርነት የከፈተበትን አቅሙንም መስበር እንፈልጋለን። »

የተመድ ዋና ጸሀፊ ፓን ኪ ሙን በሊቢያ የሚታየው ውዝግብ ውጊያ እንዳሳሳባቸው በመግለጽ ተቀናቃኞቹ ወገኖች አሁኑኑ የተኩስ አቁም ደምብ እንዲደርሱ ተማጽነዋል።

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ