የለንደኑ የእሳት አደጋ፣ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን     | ዓለም | DW | 16.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የለንደኑ የእሳት አደጋ፣ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን    

የመንግሥት ምንጮች ግን ይህን አላረጋገጡም። ከሟቾቹ መካከል ህጻናትን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ይገኙበታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:56

የለንደኑ የእሳት አደጋ፣ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን    

በዚህ ሰሞን ምዕራብ ለንደን ውስጥ በሚገኝ ባለ 24 ፎቅ የመኖርያ ህንፃ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የሞቱት ቁጥር ወደ 30 ከፍ ማለቱ ዛሬ ተነገረ። ከሟቾቹ መካከል ህጻናትን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ይገኙበታል። የእሳት አደጋው የተነሳው ከአንድ ኢትዮጵያዊ መኖሪያ ቤት መሆኑን ዴይሊሜይል ዘግቧል። የመንግሥት ምንጮች ግን ይህን አላረጋገጡም። በአደጋው የሞቱት ቁጥር  ከ150 በላይ ሊሆን ይችላል የሚሉ ግምቶች ይሰማሉ። የለንደንዋ ዘጋቢያችን ሀና ደምሴ ዝርዝሩን አዘጋጅታለች።

ሀና ደምሴ 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic