የሆለታ፣ ጊንጪና የአምቦ ዉሎ | ኢትዮጵያ | DW | 20.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሆለታ፣ ጊንጪና የአምቦ ዉሎ

ከአምቦ ከተማ ዘጋቢያችን ባደረሰን መረጃ ደግሞ “ዛሬ በርካታ ሱቆች እና የንግድ ተቋማት ተከፍተው ስራ ጀምረዋል፡፡ ከተማዋ ዳር ዳር ያሉ ሱቆች ግን አሁንም ዝግ ናቸዉ። ከተማው ውስጥ እንቅስቃሴ ይታያል፡፡” ዛሬ ባንኮች፣ ሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች፣ የባጃጅ ታክሲዎችና የህዝብ ማጓጓዣዎች ስራ ጀምረዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:36

በኦሮምያ የቀጠለው ተቃውሞ

በኦሮሚያ ክልል የቀን ገቢ የግምት ተመንን በመቃወም የንግድ ተቋማትን መዝጋትና አገልግሎቶችን ማቋረጥ ለአራተኛ ቀን መቀጠሉ ከየአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ:: ተቃውሞውን በአዲስ አበባ ያሉ የንግድ ተቋማትም መቀላቀላቸው ተነግሮአል:: ሁኔታውን በቅርበት ተከታትለናል። ረፋዱን ገፈርሳ እና ሆለታ ከተሞችን ቃኝተናል:: ከተሞቹ «መደበኛ እንቅስቃሴያቸውን እያካሄዱ» መሆኑን ከስፍራዉ መረጃ ደርሶናል። ከጊንጪ ባገኘነዉ መረጃ መሰረት “ከተማዋ የተወረረች ተመስላለች፡፡ ሁሉም ነገር ጸጥ እረጭ ብሏል፡፡ መጓጓዣ የለም፡፡ ሱቆች እና የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል፡፡ ነዋሪዎች አምስተኛ ቀናችን ነዉ ይላሉ።” የአድማ መበተኛ መሳሪያ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት በጊንጪ

መግቢያ እና መውጫ ሰፍረዋል፡፡ 

ከአምቦ ከተማ ዘጋቢያችን ባደረሰን መረጃ ደግሞ “ዛሬ በርካታ ሱቆች እና የንግድ ተቋማት ተከፍተው ስራ ጀምረዋል፡፡ ከተማዋ ዳር ዳር ያሉ ሱቆች ግን አሁንም ዝግ ናቸዉ። ከተማው ውስጥ እንቅስቃሴ ይታያል፡፡” ዛሬ ባንኮች፣ ሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች፣ የባጃጅ ታክሲዎችና የህዝብ ማጓጓዣዎች ስራ ጀምረዋል፡፡

የከተማይቱ ነዋሪዎች ለዘጋቢያችን እንደተናገሩት በአምቦ ከተማ ስራ የተጀመረው ነጋዴዎች ያነሱት ጥያቄ ተመልሶ ሳይሆን የአገልግሎት ማቆም አድማው ለሦስት ቀን የተጠራ ስለነበር ነው። ከሰኞ ጀምሮ እስከ ትላንት ድረስ የአገልግሎት ማቆም አድማ ነበር፡፡ ዛሬ በከተማይቱ ከመግቢያው ጀምሮ መሳሪያ የታጠቁ የፌደራል እና የክልሉ ፖሊስ አባላት በየቦታው ቆመው ይታያሉ፡፡ ፖሊሶችን የጫኑ ሦስት ተሽከርካሪዎች በከተማው እየተዘዋወሩ ቅኝት ሲያደርጉ ዘጋቢያችን ተመልክቷል፡፡

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ተስፋለም ወልደየስ 

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች