የህፃናት ስደተኞች መከራ | ዓለም | DW | 28.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የህፃናት ስደተኞች መከራ

የተመ የህፃናት መርጃ ድርጅት፣ «ዩኒሴፍ» በሰ/አፍሪቃ በኩል አድርገው ወደ አውሮጳ ለመግባት የሚሞክሩ ህፃናት ትልቅ አደጋ እንደተደቀነባቸው እና ብዙ እንግልትም እንደሚያጋጥማቸው አስጠነቀቀ። «ዩኒሴፍ» ይህን ይፋ ያደረገው «አደገኛው የህፃናት ጉዞ በማዕከላዊ የሜድትሬንያን ባህር፣የስደተኞች መስመር» በሚል ርዕስ ስር ዛሬ ባወጣው ዘገባው ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:59

«ዩኒሴፍ» የህፃናት ስደተኞች ስቃይ እንዲያበቃ ጠየቀ። 

በተለይ፣ ህፃናት እና ሴቶች ለወሲባዊ ጥቃት፣ ለብዝበዛ፣ እንዲሁም፣ ለሰው አሸጋጋሪዎች እና ለሊቢያ የፀጥታ ኃይላት የቁም ስቅል መከራ መጋለጣቸውን የ« ዩኒሴፍ»አስታውቋል።  እንደ ዘገባው፣ ባለፈው ዓመት ብቻ በዚሁ መስመር ከተጓዙት መካከል 4,579 ሰዎች ሰምጠው ሲሞቱ፣ ከነዚሁ መካከል ወደ 700 የሚጠጉት ህፃናት ነበሩ። የአውሮጳ ህብረት እነዚህን ለስቃይ እና መከራ የተጋለጡትህ ስደተኞች እንዲከላከል «ዩኒሴፍ» በዘገባው ጥሪ አቅርቧል። 

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic