የህፃናት ሞት በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 01.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የህፃናት ሞት በኢትዮጵያ

የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ማክሰኞ ባወጣዉ አዲስ ዘገባ እንደ ጎርጎረሳዊዉ አቆጣጠር እስከ 2030 ባለዉ ጊዜ በአለማቀፍ ደረጃ 69 ሚሊዮን ህፃናት በቀላሉ ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎች እንደሚሞቱ አትቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:55

የህፃናት ሞት

ይህ ዘገባ ለየት የሚያደረገዉ በጎርጎረሳዊዉ አቆጣጠር 2015 የወጣዉ ዘላቂ የልማት ግቦች ወይም SDG ከፀደቀ በኋላ የመጀመሪያዉ በመሆኑ እና SDG ከያዛቸዉ ከ17ቱ እቅዶች ጤናማ ማሕበረሰብ ማፍራት ላይ ዘገባዉ እንዳቶከረ በኢትዮጵያ የUNICEF የኮሙኒኬሸን አላፊ ሳሻ ቬስተርቤክ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።


ዘገባዉ አገሮችን በደረጃ ያስቀመጠ ሲሆን፣ አንጎላን በአንደኛ ደረጃ ስትቀመጥ በአገሩ እድሜያቸዉ ከአምስት በታች ከሆኑት ከየ1000 ህፃናቶች 157ቱ በዓመት ይሞታሉ ሲል አስቀምጦታል። ኢትዮጵያ ብዙ ሕፃናት ከሚሞቱባቸዉ ሐገራት 37 ደረጃ ላይ ስትገኝ በዓመት ከየ1000 ህፃናት 59ኙ እንደሚሞቱ ተጠቅሷል።

ይህ ቁጥር ምን ይናገራል ብለን በኢትዮጵያ የUNICEF የኮሙኒኬሸን ሐላፊ ሳሻ ቬስተርቤክ ጠይቀን ነበር፣ <<ዘገባዉን እንዳየዉ፣ እድሜያቸዉ ከአምስት ዓመት በታች በሆኑ ህፃናቶች ሞት ኢትዮጵያ 37 ደረጃ ላይ ትገኛለች። ግን መገንዘብ ያለብን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ለዉጦች አሉ። በሁኑ ግዜ ብዙ ህፃናቶች ረጅም ዓመት ከመቸዉም በላይ ደስተኛ ሆነዉ ይኖራሉ። በኢትዮጵያም እድሜያቸዉ ከአምስት በታች የሆኑት ህፃናቶች ሞት በሁለት ሶስተኛ እንደቀነሰ፣ በጎርጎሮሳዊያኑ 1990 ከ1000 ህፃናቶች 204 ሲሞቱ እንደነበር ይህም በ2012 ቀንሶ ከ1000 ህፃናቶች ወደ 68 ወርደዋል።>>


ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህጻናት በቀላሉ ሊከላከል በሚችል በሽታ ሲሞቱ ያሳዝናል የምሉት ሳሻ ይሄንንም ለመከላከል ብዙ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል። << እኔ አጠናክሬ የምያምነዉ የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች፣ UNICEFን ጨምሮ ግልፅ የሆነ ምርጫ ማድረግ አለባቸዉ። ወደ ዋላ የቀሩ ህፃናቶችን ኑሮና ጤናን ለማሻሻል ገንዘብ መመደብ እና እንዲለወጡ ማድረግ አለብን፣ ካልሆነ ግን በ2030 ለሚያጋጥመን መከፋፈል እና ፍታዊ ያልሆነ ዓለምን መቀበል አለብን። አሁን ምርጫ አለን፣ ግደታም አለብን። መንግስትና ሌሎች ድርጅቶች ግዴታ ቢኖርባቸዉም ግን ሁሉም ለለዉጥ መሳተፍ አለባቸዉ፣ ይህም የሚያጠቃልለዉ አስተማርዎች፣ የጤና መኮንኖች፣ ቤተሴብ፣ የልጆች ጠባቂዎች እና ህፃናቶች ራሳቸዉን ነዉ። ሁላችንም መብትና ግዴታ አለብን።>>


በዝህ ጉዳይ ላይ በዶቼ ቬሌ ድረ ገፅ ላይ ዉይይት አካሄዴን ነበር፣ አብዛኛ አስተያየት ሰጭዎችም መንግስት የመሕበረሰቡን የኑሮ ዋስትና ማሻሻል እንዳለበት እና ሌሎችም ሐላፊነታቸዉን እንዲወጡ ጠቅሰዋል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic