የህጻን መሐመድ አብዱላዚዝ የህያ ጉዳይ | ዓለም | DW | 27.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የህጻን መሐመድ አብዱላዚዝ የህያ ጉዳይ

በሐኪሞች ስህተት ለዚህ የዜና ችግር የተዳረገው ህጻን ጉዳይ በ9 ዓመቱ ውሳኔ ቢያገኝም ተፈጻሚ አልሆነም። እስከ ዛሬ ተስፋ ሳይቆርጡ የልጃቸውን መንቃት ሲጠባበቁ የቆዩት ወላጅ እናቱ አሁን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ መወሰናቸውን ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:32

የህጻን አብዱላዚዝ ቤተሰቦች ውሳኔ

የመተንፈስ ችግር የነበረበት ሳውዲ አረብያ የተወለደው ህጻን መሀመድ አብድልአዚዝ የህያ በሳውዲ አረብያው ጅዳ በሚገኘው ሆስፒታል ከተካሄደለት ቀዶ ህክምና በኋላ ሳይነቃ 12 ዓመታት ተቆጥረዋል። በሐኪሞች ስህተት ለዚህ ችግር የተዳረገው ህጻን ጉዳይ በ9 ዓመቱ ውሳኔ ቢያገኝም ተፈጻሚ አልሆነም። እስከ ዛሬ ተስፋ ሳይቆርጡ የልጃቸውን መንቃት ሲጠባበቁ የቆዩት ወላጅ እናቱ አሁን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ መወሰናቸውን ለዶቼቬለ ተናግረዋል። የመሀመድ ጉዳይ ፍትህ እንዲያገኝ ወላጆቹ ያደረጉት ሙከራ እስካሁን ውጤት ባያስገኝም ክትትሉ ግን እንደቀጠለ በሳዑዲ አረብያ ጅዳ የኢትዮጵያ ቆንሰላ ኃላፊ አምባሳደር ውብሸት ደምሴ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ነብዩ ሲራክ ከጅዳ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ነብዩ ሲራክ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic