የህዳሴ ግድብ ጥናትና የሶስትዮሹ ስምምነት | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 13.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የህዳሴ ግድብ ጥናትና የሶስትዮሹ ስምምነት

ሱዳን፣ ግብፅ እና ኢትዮጲያ ለብዙ ግዜ እየተንከባለለ ከመጣ ድርድር በኋላ በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ታህሳስ 29 2015 ካርቱም ሱዳን ሊይ Declaration of Prinicples ወይም የመሰረታዊ መ መርሆዎች ሰነድ ተብሎ የምጠራዉን ሰነድ መፈራረማቸዉ ተዘግቧል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:28

የሶስትዬዎሹ አገሮች ስምምነት

እስካሁን ድረስ ስምምነቱን አጓቷል ተብሎ በዋናነት የሚጠቀሰዉ የግድቡን ሁኔታ እንድያጠኑ ተመርጠው ከነበሩት ሁለት ኩባንንያዎች ዴልታሬስ የተባለው የኔዘርላንድ ኩባንያ፣ በፈቃዱ ራሱን ከጥናቱ ማግለሉ ነው ። ከዚህ ሌላ ሦስቱ አገራት ኩባንያዉ የወሰደዉን እርምጃ ለመረዳትና ወደ ጥናቱ እንዲመለስ ለማግባባት ያደረጉት ጥረት ለድርድሩ መጓተት ተጨማሪ ምክንያቶች ናቸው የሚሉ ባለሙያዎች አሉ። ዴልታሬስን ለመመለስ የተደረገዉ ጥረት ሳይሰካ ሲቀር ጥናቱን ለማካሄድ ፍላጎት ያሳይ የነበረ ኣርቴላይ የተባለዉ የፈረንሳይ ኩባንያ ሃላፊነቱን ከዴልታሬስ ተረክቦ 30 በመቶዉን የጥናቱን ስራ እንድያከናዉን፣ ቀሪዉን 70 በመቶ ጥናት ደግሞ BLR የተበለዉ የፈረንሳይ ኩባኒያ እንድቀጥልበት አገሮቹ ተስማምተዋል ። ዋነኛዎቹ ጉዳዮች እነዚህ ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪም ሦስቱ አገሮች ሰነዱ በአስቸኳይ ተግባራዊ በሚሆንበት መንገድ ላይም ተነጋግረዋል ። በሶስተኛና በአራተኛ ደረጃ የተወያዩት ደግሞ ጥናቱ ከታካሀደ በዋላ በተፋጠነ ሁኔታ ስራ ላይ እንድዉሊና በአገራቶቹ መካከል እምነት የመገንባት ስራ እንድሰራ ተስማምቶት እንደተለያዩ በኢትዮጵያ የዉሃ፣መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር እንጅኔር ተሾመ አጥናፌ ያስረዳሉ።


የየአገሮቹ የዉጭ ጉዳይ እና የዉሃ ሚኒስቴሮች፣እንዲሁም የቴክኒክ ኮሚቴዎችን በተሳተፉበትና ከታህሳስ 27 እስከ 29 በተካሄደ ስብሰባ ። Declaration of Prinicples የመሰረታዊ መርሆች ሰነድ መፈራረማቸዉ እንደ አንድ ትልቅ ስኬት ተወስዷል። ሰነዱ በዉስጡ ከያዘቸዉ 10 ዋና ዋና መሰረታዊ መመርያዎች መሃል ሶስቱ አገሮች የአባይን ዉሃ ሲጠቀሙ <<ታላቅ>> የተባለዉን ጉዳት አለማድረስ፣ ከደረሰ ደግሞ ተገቢዉን ካሳ የመክፈልና እና ካዛም አልፎ ግድቡን በዉሃ ለመሙላት እና ስራ ላይ ለማዋል የአለማቀፍ የቴክኒክ ባለሙያዎች እና የTripartite National Technical Committee ወይም የሶስትዬዎሹ የብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ ምክሮችን መከተል እና መቀበል እንዳለበቸዉ ያሳስባል። በተጨማርም የግብጽ እና የስዳን የዉሃ ኮታ እና ግድቡ በአከባቢ፣ በኤኮኖሚ እና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚፈጥራቸውን ጫናዎች የተመረጡት ኩባንያዎች በ15 ወራት ዉስጥ አጥነተው እንዲጨርሱም ሰነድ ይጠይቃል።


እንጅንየር ተሾመ አጥናፌ ከዚህ በፊት የዓለም አቀፍ አጥኚዎች ቡድን የህዳሴ ግድብ ጥናቶችን እንደገመገመና እና በመጨረሻም ሪፖርቱን እንዳቀረበ ተናግረዋል። የሪፖርቱን ዋና ዋና ይዘቶች የነበሩት የhydrosimulation ወይም ዉሃ ሙሌት በተመለከተ እና ግድቡ የአከባብ እና ማህበራዊ ሁኔታዎች ላይ ያለዉን ተፄኖ የተመለከተ ነዉ ይላሉ።
ለመሆኑ የሁለቱ ኩባንያዎች ጥናት የተለየ ትኩረት ምንድንነው? ተብሎ እንጅኔር ተሾሜ አጥናፌ ስጠየቁ ሁለቱም ኩባንያዎች ዋና የጥናት አከባብ የግድቡ ግንባታ ከተተናቀቀ በዋላ ዉሃ ሙሌት እንዴት እንደሆነ እና እንዴት ስራ ሊይ መዋል እንደምችል ነዉ ይላሉ። ሌላኛዉ ደግሞ ይላሉ እንጅኔር ተሾሜ አጥናፌ ግድቡ በመንገባቱ በታችኛዉ የዉሃ ተፋሰስ አገሮች ላይ ሊያመጣ የምችለዉን ጉዳት እና አከባብ ላይ ያለዉን ተፄኖ ይመለከታል።


የመሰረታዊ መርሆቹ ሰነድ ዉሃ ሙሌትን በተመለከተ ሦስቱ አገሮች ፣የቴክኒክ ኮሚቴዎች የሚያቀርቡትን የጥናቱን ዉጤት ስራ ላይ እንደሚያዉሉ ያሳስባል። የዉሃ ሙሌቱ ም ሆነ የማህበራዊ እና አካባቢያዊ ተፅእኖው ጥናት ሲካሄድ ጥቅም ላይ የሚውሉት ሳይንሳዊ ዘዴዎች ምንድን ናቸው ? እሄን በተመለከተ እንጅኔር ተሾሜ ስያብራሩ፣ BRL የተባለዉ ኩባኒያ ገና የጥናት ስራ የምያሳይ ሰነድ ስያቀርብ የራሱን የጥናት ዜዴዎች እና ባለሙያዎች ተጠቅሞ ስራዉን እንደምያከናዉን እንደሆነ እና መጀመርያም ኩባኒያዎቹ መመረጥ የቻሉት የምጠቀሙት ሳይንሳዊ ዜዴዎች አሳማኝ መሆኑን ታይቶ ነዉ ይላሉ።


ካርቱም ላይ የተካሄደዉን ስምምነት ተከትሎ በአንዳንድ መደበኛ መገናኛ ብዙሃንም ሆነ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እትዮጲያ ግድቡን በዉሃ እንደማትሞላ ከግብፅ ጋር ተሰማምታለች የሚባለዉን እንጅኔር ተሾሜ ዉድቅ አድርጎዋል። ለጥናቱ የተሰጠዉ 15 ወራት የጊዜ ገደብ እንደ እንጅኔር ተሾሜ አጥናፌ ገለፃ፣ በጎርጎሮሳዊው መጋቢት 2015 ካርቱም ላይ ሶስቱም አገሮች የደረሱበት ዉሳኔ ነዉ ። ስራዉ የሚከናወነው BRL ባቀረበዉ ዘዴ እና አሰራር መሰረት ስለሆነ፣ አርቴሊያም የሚሰረዉ BRL በምያቀርበዉ መንገድና እና አሰራር ይሆናል ማለት ነዉ፣ ስሉ እንጅነሩ ያስረዳሉ። BRL ጥናቱን በ11 ዋራት ዉስጥ አጠናቅቃለዉ ሲል ያቀረበዉ የጥናት ሰነደ እንዳለም አስረድተዋል ። ጥናቱ ከተጠናቀቀ በኋላም ሦስቱ አገሮች ተገናኝተው፣ ለ4 ወራት ውጤቱን ይገመግማሉ። እስካሁን አጥኝዎቹ ጥናቱ የሚፈጀውን የገንዘብ መጠን እዳልቀረቡ እንጅኔር ተሾመ አጥናፌ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። የቴክኒክ ኮሚቴዎች ብቻ የሚያሳትፈው ቀጣዩ ስብሰባ ከጥር 22 እስከ 25, 2016 በካይሮ፣ ግብፅ ፣እንደሚካሄድ ፣ይህ ቀጠሮ ሊለወጥም እንደሚችል ተነግሯል። በዚህ ስብሰባም ኩባንያዎች የሚያቀርቡትን የገንዘብ ጥያቄም ሆነ የጥናቱን እቅድ ለመገምገም እና አንድ አቋም ላይ ለመድረስ እንዳቀዱ እና እንደተስማሙም ይናገራሉ።


BRL የተባለዉን ኩባንያ ምን አይነት ሳይንሳዊ ዘዴዎች ተጠቅሞ ጥናቱን ሊያከናዉን እንዳቀደ ጠይቀን ነበር። ይሁን እንጅ የኩባኒያዉ የግብይት ልማት ሃላፊ እሳቤላ ሁቢቼ ለዶቼ ቬሌ በላኩት እሜል ጥናቱን የሚመለከቱት ስምምነቶች ስላለቁ ባሁኑ ሳዓት በዚህ ጉዳይ ላይ መናገር እንደማይችሉ መልስ ሰጥተውናል። አርቴላይም ስለዚሁ ጉዳይ ለመናገር ፈቃደኛ አለመሆናኑን አሳዉቆዋል።

መርጋ ዮናስ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች