የህዳሴ ግድብ ግንባታ 3ኛ ዓመት | ኢትዮጵያ | DW | 23.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የህዳሴ ግድብ ግንባታ 3ኛ ዓመት

ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዕድገትና የለውጥ እቅድ ለማሳካት አስፈላጊ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የኤሌክትሪክ አቅርቦት ትልቁን ሚና ይዞዋል። በኢትዮጵያ የኤሌክትሪኩን አገልግሎት ዘርፍ የማስፋፋቱ ስራ ከተጀመረች ብዙ ዓመታት ቢሆነውም ፣ ውጤቱ እስካሁን የሚፈለገው ደረጃ ላይ ገና አልደረሰም።

ኢትዮጵያ የሕዝቧን ፍላጎት እና ኢንዱስትሪዎችን የማስፋፋት ጥረቷን ለማርካት አሁን ያሏት ግድቦች በቂ እንዳልሆኑ በመገንዘብ በዓባይ ወንዝ ላይ 6,000 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል የሚባለውን የህዳሴ ግድብ ግንባታን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጀምራለች።

Blue Nile, Map, english

እአአ በ2015 ዓም በተወሰነ ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል የሚባለው እና እአአ በ2017 ዓም እንደሚጠናቀቅ የተነገረለት የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አሁን ሦስተኛ ዓመት የሆነበትን ምክንያት መነሻ በማድረግ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እና ሂደቱ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ተወያይተንበታል።

አርያም ተክሌ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic