የህዝብ ጤንነትና ሀኪሞች | ኢትዮጵያ | DW | 01.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የህዝብ ጤንነትና ሀኪሞች

የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት፤ በቅርቡ ያወጣው የመጠርዝር ጥናት ውጤት እንደሚያስረዳው፤ በህክምና ርዳታ የሰዎች ዕድሜ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመራዘም ላይ ነው። ባለፉት 2 ዐሠርተ ዓመታት በዓለም ዙሪያ በአማካይ የ 9 ዓመት ጭማሪ አሳይቷል።

የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት (WHO) እንደገለጸው ፣ እ ጎ አ በ 1990 እና 2012 መካከል፤ በኢትዮጵያና ሌሎች 5 ሃገራት በአማካይ ከ 10 ዓመት በላይ የሰዎች ዕድሜ እንዲጨምር ለማድረግ ተችሏል። ከሰሃራ በስተደቡብ በሚገኙ የአፍሪቃ አገሮች፤ ኢትዮጵያ ፣ የ 20 ዓመት ጭማሪ ያሳየችውን ላይቤሪያን በመከተል ፤ በ 9 ዓመት ጭማሪ ፣ አማካይ ዕድሜ ከ 45 ወደ 64 ከፍ እንዲል ማብቃቷ ተጠቅሷል። ዶቸ ቬለ ፤ የህዝብ ጤንነትና ሀኪሞች፤ በሚል ርዕስ ፣ በተወሰነ ዘርፍ የተመዘገበው የተሻሻለ ውጤት በሁሉም እንዴት ሊቀጥል እንደሚችል፣ ስለ ህሙማንና ሀኪሞች ግንኙነት ባለሙያዎችን አወያይቷል ።

ተክሌ የኋላ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic